የዓለም የራድዮ ቀን
ሰኞ፣ የካቲት 6 2015በኢትዮጵያ፣ራዲዪ በየቤቱ መረጃን በመድረስ ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ የመገናኛ ብዙሀን ዘርፍ ነው። በቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት በ 1928 መስከረም 2 የተጀመረው የራዲዪ ፕሮግራም ስርጭት አገልግሎት እስካሁን በ አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ዋነኛው የመረጃ ምንጭ በመሆን እያገለገለ ነው። በተለይ ከተማ ቀመስ ከሆነው አካባቢ ውጭ ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ራዲዮ ዋነኛ የመረጃ ምንጫቸው ነው። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን አገልግሎት የራዲዮ ስርጭት በሀገሪቱ ከተጀመረበት ከ 19 28 ጀምሮ ላለፉት 87 አመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ 83 አጭር በመካከለኛ በረጅም ሞገድ እንደዚሁም ለኤፍ ኤም ራዲዮ ስርጭቶች ፍቃድ ሰጥቷል
ራዲዮ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች በትራንስፖርት እንደዚሁም በገበያ ስፍራዎች ተዘውትሮ ይደመጣል በአዲስ አበባ ያነጋገርናቸው ግለሰቦች አሁንም ምርጫችን ራዲይ ነው ይላሉ
«ስራዩ ከእንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ምርጫዪ ራዲዮ ነው አዳዲስ እና ትኩስ መረጃዎች አእገኝበታለሁ»«‘እኔ በግሌ ከራዲይ የተሻለ መረጃ አገኛለሁ ብዪ አስባለሁ ምክንያቱም በየሰአቱ እና በየደቂቃው የተለያየ ጣቢያ ስታዘዋውሪ የምታገኝው መረጃ አዳዲስ እና ፈጣን ነው።»በማለት ራድዮን ምርጫቸው ያደረጉበትን ምክንያት ያስረዳሉ።
በኢትዮጵያ ከአፋር ክልል በስተቀር ሁሉም ክልሎች የየራሳቸው የህዝብ ራዲዪ ስርጭት አገልግሎት አላቸው ።ያም ሆኖ የአፋር ዩንቨርስቲ ራዲዮን ጨምሮ ሁለት የማህበረሰብ ራዲዮዎች በክልሉ እንደሚገኙ እቶ ደሴ ከፍአለ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነት ጉዳዪች ዳይሪክቶሪት ለዶቼቬለ ተናግረዋል።አቶ ደሴ እንዳሉት እስካሁን ለ83 የተለያዪ ራዲይ ጣቢያዎች የባለስልጣኑ መስሪያቤት ፍቃድ ሰጥቷል ። በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ብቻ 22 የራዲዮ አገልግሎት የሚሰጡት ተቋማት ዝግጅታቸውን ለአድማጮቻቸው ያደርሳሉም ብለዋል።አቶ መሀመድ ሲራጅ የአዋሽ ኤፍ ኤም 90፣ 7 ራዲዮ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው“ በራዲዮ የሚሰራጭ መልዕክትን ሁሉም ሰው በቀላሉ ሊያገኘው ይችላል በዚህ ላይ ወሰን የለውም ማድመጥ ስለሆነ ወሰንም ገደብም የለውም »የአለም የሪዲዮ ቀን ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 12 ኛ ግዜ ታስቦ ውሏል።
ሀና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ