ማስታወቂያ
በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎችና ባለድርሻ አካላት አገራዊ መግባባትንና ዘላቂ መፍትሔዎችን እንዲያመጡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ። አብን በአማራ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር ተባብሶ መቀጠሉን አስታዉቋል
የጀርመኑ መራሔ መንግስት ፍሬድሪክ መርስ አገራቸዉ በዮርዳኖስ እርዳታ ሰብአዊ ቁሳቁስና ምግብን በአየር ወደ ጋዛ ሰርጥ ለማድረስ ማቀድዋን ተናገሩ። በሌላ በኩል መራሔ መንግሥት ሜርስ በአውሮጳ ህብረት እና በአሜሪካ መካከል የተደረገውን የንግድ ስምምነት በደስታ ተቀብለዉታል።
ታይላንድ እና ካምቦጂያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ስምምነቱ ተጥሶ ውጊያ ማገርሸቱ ተሰማ። ባለፈዉ ሳምንት ቅዳሜ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታይላንድን እና የካምቦጂያን መሪዎች ባነጋገሩበት ወቅት ሁለቱ ሃገራት የጀመሩትን ጦርነት እስካላቆሙ ድረስ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ሃገራቸዉ ያላትን የንግድ ስምምነቶች እንደሚያቆሙ ዝተዉ ነበር።