ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲሱ ፕሬዚደንት ምን ይጠበቃል? አንድ ለአንድ፥ ቃለ መጠይቅ
ዓርብ፣ ጥር 23 2017ማስታወቂያ
በቅርቡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲስ ፕሬዚደንት መርጧል ። የአገራቸውን ስም በዓለም መድረክ ያስጠሩ በርካታ ብቃት ያላቸውን አትሌቶች ፌዴሬሽኑ የማፍራቱን ያህል በተለያዩ አወዛጋቢ ጉዳዮችም ስሙ በተደጋጋሚ ይነሳል ።
አትሌቶችን በዓለም አቀፍ መድረኮች ተፎካካሪ እንዲሆኑ በመምረጥ ሒደት አድልዎ ይፈጸማል፤ በኦሎምፒክ ውድድሮች ወቅትም ተደጋጋሚ በደሎች ይደጋገማሉ የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ ። ይህን እና ሌሎች የፌዴሬሽኑን ስሞች በበጎም ሆነ በመጥፎ የሚያስነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ከአዲሱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አትሌት ስለሺ ሥኅን ጋር ማንተጋፍቶት ስለሺ ቀጣዩን ቃለ መጠይቅ አድርጓል ።
አትሌት ስለሺ ሥኅን፦ በጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር በ2004 በአቴንስ እንዲሁም በ2008 በቤጂንግ ኦሎምፒክ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ነው ። በዓለም ሻምፒዮና ለሦስት ጊዜያት የብር አንድ ጊዜ የነሐስ ሜዳሊያ ካገኛቸው ድንቅ ድሎች የሚጠቀሱለት ናቸው ። አትሌት ስለሺ ሥኅን በሦስት ሺህ፣ በአምስት ሺህ እንዲሁም በዐሥር ሺህ ሜትር በዓለም አቀፍ መድረኮችም ይታወቃል ።
ሙሉ ቃለ መጠይቁን እንድታደምጡ እንጋብዛለን ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ፀሐይ ጫኔ