የአብን ሕዝባዊ ስብሰባ በፍራንክፈርት
ቅዳሜ፣ ጥር 30 2012ለኢትዮጵያ ኅልውናና አንድነት ከሌሎች የአገሪቱ ብሄረሰቦች ጋር ከፍተኛ የሕያወት መስዋዕትነት የከፈለው የአማራ ሕዝብ በተለይም ባለፉት አምስት አስርተ ዓመታት በተከፈተበት የፈጠራ ትርክትና ብሄር ጠል ተኮር ዘመቻ ማንነቱን ሳይወድ በግድ እንዲቀይርና እንዲፈናቀል በማድረግ ከፍተኛ የህልውና አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ ተደርጓል ብለዋል አመራሮቹ:: በተለይም ከክልሉ ውጭ በሚኖረው ሰፊው የአማራ ተወላጅ ላይ የሚፈፀመው ግድያ እና ማፈናቀል እጅግ እየከፋ በመሄዱ በማንነቱ ተደራጅቶ ህልውናውን ማስጠበቅ አማራጭ የለውም ተብሏል::የውይይቱ ተሳታፊዎች በክልልሉ ተወላጅ ተማሪዎች እገታ ላይ አዴፓና የፌደራል መንግሥቱ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ አይደሉም ሲሉም ወቅሰዋል::ከሰኔ 16ቱ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ በፈጠራ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸዋል ያሏቸውን የንቅናቄው አመራሮችና ደጋፊዎችም ለማስፈታት በአገር ውስጥም በውጭም የተደራጀ ሰላማዊ የተቃውም እንቅስቃሴ እንደሚደረግ ያስታወቁ ሲሆን አሁን ባለው የሰላም ዕጦትና አለመረጋጋት አገራዊ ምርጫውን ማካሄድ አዳጋች ቢሆንም ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሚካሄድ ከሆነ አብን ከፍተኛ ተሳትፎ እንደሚያደርግም አመራሮቹ ገልፀዋል::ከዚህ ሌላ ኃላፊው በስዊድን ከኢትዮጵያውያን ጋር ያደረጉት ተመሳሳይ ስብሰባ እና ከስዊድን መንግሥት የፓርላማ ተወካዮች ጋር ያካሄዱት ውይይትም እጅግ ስኬታማ ነበር ነው ያሉት::
እንዳልካቸው ፈቃደ
አዜብ ታደሰ