የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ በሰዎች ተወሯል
ሐሙስ፣ መጋቢት 23 2013ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሀረርጌ እና ሶማሌ ክልል ፋፈን ዞኖች የሚገኘው የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ስልሳ በመቶ የሚሆነው መሬቱ በሕገወጥ መንገድ በሰዎች መያዙ በዝሆን እና ሌሎች የዱር እንስሳት ህልውና ላይ አደጋ መፍጠሩን የመጠለያው ፅሕፈት ቤት የቀድሞ ኃላፊ ገለፁ፡፡ የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያን ለሶስት ዓመታት ያህል በኃላፊነት ያስተዳደሩት የመጠለያው ፅሕፈት ቤት የቀድሞ ኃላፊ አቶ አደም መሀመድ ለዶቼ ቬለ DW በስልክ በሰጡት መረጃ ባለፉት አመስት እና ስድስት ዓመታት መጠለያው ላይ በተደረገ ሕገወጥ የመሬት ወረራ እስከ ስልሳ በመቶ የሚሆነው መሬት መያዙን ገልፀዋል፡፡
መሳይ ተክሉ
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ