ሰብዓዊ መብቶችሰሜን አሜሪካ
በስደተኞች ጉዳይ የትራምፕ ርምጃና ተቃውሞው
ሰኞ፣ ሰኔ 2 2017ማስታወቂያ
በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በካሊፎርኒያ ግዛት የተካሄደው የስደተኞች አሰሳ ያስከተለው ተቃውሞ በጸጥታ አስከባሪዎች እና ሰልፈኞች መካከል ግጭት አስከትሏል። ፕሬዝደንቱ ከበርካታ አስርት ዓመታት በፊት የጥቁሮችን መብት ለማስከበር ፌደራል መንግሥት የወሰደውን ብሔራዊ ዘብን ያሰማሩበት እርምጃ ከካሊፎርንያ ግዛት ክስ አስከትሏል። ሎስ አንጀለስ ከተማ ላይ የአሜሪካ የኢሚግሩሽንና የጉምሩክ ፖሊሶች ከዓርብ ጀምረው ሕገወጥ ስደተኞች ይገኙባቸዋል ተብለው በሚገመቱ የተለያዩ የንግድ ስፍራዎች ፍተሻ ማካሄዳቸው በአብዛኛው በስደተኛ ነዋሪዎች ብዛት የሚታወቁትን የሎስ አንጀለስና አካባቢውን ከተሞች ነዋሪዎች አስቆጥቷል። ሁኔታው በምን ደረጃ ላይ ይገኛል፤ በቀጣይስ ወዴት ያመራል? የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆኗል። ከዋሽንግተን ዲሲ አበበ ፈለቀን በጉዳዩ ላይ በአጭሩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
አበበ ፈለቀ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ