የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሚና ለሰላም
ሐሙስ፣ ኅዳር 20 2016የሲቪል ማኅበረሰቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰላም ችግር ለመፍታት የተቀናጀ፣ አካታችነትን ያረጋገጠ ብሎም ትርጉም ያለው ሥራ ለመሥራት ወደ ሕዝቡ በመግባት መሰረታዊ የሆነ የማኅበረሰባዊ ንቅናቂ ማካሄድ አለበት ተባለ ። ይህ የተነገረው የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከ ደህንነት ጥናት ተቋም ጋር በመሆን ባዘጋጀው መድረክ ነው ።
“የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በመረጃ ላይ የተደገፈ የሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በኢትዮጵያ ያላቸውን አስተዋጽኦ ማጠናከር” በሚል እሳቤ የተሰናዳው መድረክ በኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበራት በቤተ መንግስቱ እናበቤተ ማህበሩ መካከል ያለውን ችግር ለመፍታት ወደህዝቡ ወርደው በሕዝቡ ባህል እና እሴት መስራት ይኖርባቸዋል ተብልዋል። አሁን ለሰላም ግንባታው ሂደት በኢትዮጵያ ያለው የሰላም እጦት መንሳኤ ምን እንደሆነ መጠናት አለበት ሲሉ ለ DW የተናገሩት የፅሁፍ አቅራቤ ፕሮፊሰር ቃለወንጌል ከኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት ናቸው ።
የሲቪል ማኅበራት የተለያዩ የገንዘብ ድጎማዎችን ጠብቀው ያዝ ለቀቅ ያለ ሥራ ከመስራት ወደ ሕዝቡ በመውረድ የተለያዩ የኅበረሰብ ክፍሎችን ፣ የሀይማኖት ተቋማትን እና የሰራተኛ ማህበረሰብ ሁሉ በማሰተፍ ራሱ የሆነ ጠንካራ ቁዋንቁዋ ያለው ታማኝ ማህበር መሆን ይገባዋል ተብልዋል ። እስካሁን በሲቪል ማህበራት በኤትዮጵያ በስላም ግንባታ ላይ የተሰራ ስራ በጣም አናሳ እንደሆነ በቀረበ ሲሆን አሁን በኢትዮጵያ በጦርነት እና በግጭት ተውጥራ ባለችበት ወቅት የሲቪል ማኅበራት ከሰላም ግንባታ በፊት ግጭቶች ለማስቆም መሥራት ነው ያለብን ሲሉ ታዳሚዎች ተናግረዋል።
በኢትዮጵያበየቦታው ለሚካሄደው የግጭት ምክንያት አንዱ መዋቅርዊ እንደሆነ እየታወቀ መንግስት በመዋቅሩ ወስጥ ያለውን ችግር ለመፍታት ይሰራል ማለት የማይታሰብ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት አቅም ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ነው የሲቪል ማኅበር በተጣሉት ወግኖች መሀል በመግባት ያስታርቃል ያግባባል የማኅበረሰቡን እሴት በማጠናክር እና የሕግ የበላይነት እንዲከበር በማድረግ ወሳኝ ሚና መጫወት ይችላል። ይህ የሚሆነው ግን አሁን እዚህም እዛም ያለውን ግጭትን እንዴት እናጠፋለን በሜለው ላይ ትኩረት አድርጎመስራት ሲችል እና የሲቪል ማኅበረስብ ከመጣው ጋር ማጨብጨቡን አቁሞ የራሱን አቁዋም ሲይዝ ነው ተብሎዋል ።
ሐና ደምሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ