የሰላም ስምምነቶች እስኪፈፅሙ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ቁመናውን ጠብቆ እንደሚቆይ መነገሩ
ሰኞ፣ ሐምሌ 28 2017የሰላም ስምምነት ይዘቶች እስኪፈፅሙ እንዲሁም የሚጠበቀው የሰራዊት ስንብት ሂደት እስኪተገበር ድረስ 'የትግራይ ሰራዊት' ወታደራዊ ቁመናው ጠብቆ እንደሚቆይ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ። ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የፌደራሉ መንግስት ሐላፊነቱ እንዲወጣም ጀነራል ታደሰ ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ አወንታዊ ምላሽ ማግኘታቸው ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጋር የተወያዩ የትግራይ ማኅበረሰብ ዲፕሎማሲ አባላት አስታውቀዋል። የትግራይ ኃይሎች ጥቃት ደረሰብን አሉ
የትግራይ ሐይሎች የተለያዩ አሃዱዎች የሚያስመርቋቸው የጦርነት ውሏቸውን የሰነዱ መፅሓፍቶች ለማስመረቅ በሚሰናዱ ዝግጅቶች ወታደራዊ ሰልፍ እና ሌሎች ትርኢቶች የሚካሄዱ ሲሆን በትላንትናው ዕለትም በውቅሮ ከተማ ተመሳሳይ ትእይንት ቀርቧል። በዚሁ መርሐ ግብር የተገኙት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ የሰላም ስምምነት ይዘቶች እስኪፈፅሙ እንዲሁም የሚጠበቀው የሰራዊት ስንብት ሂደት እስኪተገበር ድረስ 'የትግራይ ሰራዊት' ወታደራዊ ቁመናው ጠብቆ እንደሚቆይ ተናግረዋል።
እየተደረጉ ያሉት ወታደራዊ ስልጠናዎች የጦርነት ዝግጅት አልያም ወታደራዊ ተልእኮ ለመፈፀም አይደሉም ያሉት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ ሰራዊቱ እስካለ ድረስ ግን ስልጠናዎች ይቀጥላሉ ሲሉ አክለዋል። ስለ ፕሪቶሪያው ግጭት ማቆም ስምምነት የህወሓት መግለጫ
ጀነራል ታደሰ ወረደ "በሰራዊት ውስጥ የሚደረግ ስልጠና፥ ሰራዊቱ እስካለ ድረስ የማይቋረጥ፣ አስፈላጊነቱ እየቀነሰ ሲሄድ ደግሞ የሚቋረጥ ይሆናል። ይሁንና ሰራዊቱ እንዳለ ሆኖ ስልጠና እንዳይወስድ ማድረግ ግን ችግር የሚፈጥር ነው። ስለዚህ ስልጠና አሁን ይሁን ለወደፊቱ፥ የሰራዊቱ መቆየት አላማዎች እስካሉ ድረስ የሚቀጥል ይሆናል" ብለዋል። የትግራይ ጥያቄዎች መመለስ ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ ጥያቄዎቹ ግልፅ ናቸው፣ የትግራይ ግዛት ወደ ነበረበት እንዲሁም ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው መመለስ እንዳለባቸው ተናግረዋል። በትግራይ ያሉ ሐይሎች ሳይበተኑ እንዲቆዩ የሚያደርጉ እንዲሁም ለጦርነት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ አጀንዳዎች የፌደራሉ መንግስት መፍትሔ ሊሰጥቦቸው እንደሚገባም ጀነራል ታደሰ ጨምረው ገልፀዋል።
ጀነራል ታደሰ "አስተማማኝ ሰላም ለመፍጠር በሚመለከታቸው አካላት በኩል በተለይም በፌደራሉ መንግስት በኩል አስፈላጊ ስራዎች እንዲሰራ፥ የጦርነት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ እንዲሁም ሰራዊቱ የግድ እንዲቆይ እያደረጉት ያሉ ምክንያቶች እንዲፈቱ ለማድረግ ከፍተኛ ትብብር እንደሚያደርግ እምነት አለኝ" ሲሉ ተናግረዋል። በትግራይ ክልል በተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ይረጋገጥ ፤ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ያለው ፍጥጫ ለመሸምገል በማለም ከትግራይ ወደ አዲስአበባ በመጓዝ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ጋር የተወያዩት የትግራይ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት፥ ጦርነት ለማስቀረት በሚያደርጉት ጥረት ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል አወንታዊ ምላሽ ማግኘታቸው ገልፀዋል። ወደ አዲስአበባ በመጓዝ ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጋር ከተወያዩት አንዱ ሓጂ መሓመድ ካሕሳይ "ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አግኝተናቸዋል። በትግራይ የሚተኮስ ነገር እንደማይኖር ላረጋግጥላችሁ እችላለሁ ብለዋል። ከትግራይ በኩልም ተመሳሳይ ነገር ተነገረን። በሁለቱም በኩል ይህ አረጋግጠናል" ሲሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ
ፀሐይ ጫኔ