እንወያይ፤ 40ኛ ዓመት የእርዳታ ኮንሰርት-በኢትዮጵያ ዛሬም ያልተመለሰዉ የምግብ ዋስትና ጥያቄ
ሰኞ፣ ሐምሌ 21 2017ኢትዮጵያ የዛሬ 40 እና 50 ዓመት ደርሶባት የነበረዉን አስከፊ ድርቅ እና እና ከፍተኛ ረሃብ ተከትሎ፤ እርዳታን ያሰባሰቡት የዓለም ታዋቂ ሙዚቀኞች ባለፈዉ ሰሞን 40ኛ ዓመቱን ሲክሩ ኢትዮጵያ ዛሬ በምን ሁኔታ ዉስጥ ሆና ይሆን? የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ። ያዝያን ዘመኑ ድርቅ እና ከፍተኛ ረሃብ የኢትዮጵያን ገፅታ በእጅጉ ቀይሮታል። ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ለዘመናት ረሃብ ድርቅ ከሚለዉ ጋር ስሟ አብሮ ሲጠራ ዘልቋል። ዛሬስ? ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና ዝግጅትዋ ምን ያህል ጠንካራ ናት? ከዚያን ጊዜዉ አስከፊ ድርቅስ ምን ተሞክሮ ተገኘ?ደቡብ ወሎ ዞን 380 ሺህ ህዝብ የምግብ ድጋፍ ይፈልጋል ተባለ
ኢትዮጵያ ዉስጥ በአሁኑ ወቅት የኑሮ ዉድነት ግጭት ጦርነት፤ ብሎም ጎርፍ ድርቅ ከመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋ ጋር ተደምሮ ለምግብ እጥረት የተጋለጠው ኅብረተሰብ ቁጥሩ በርካታ እንደሆነ ይገለጻል። ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ የተለያዩ የረድኤት ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ይሰጡት የነበረውን ድጋፍ መቀነሳቸዉ አልያም ማቋረጣቸዉ በእርዳታ ይኖሩ የነበሩ ብሎም እርዳታን ይጠብቁ የነበሩ የጦርነት እና የድርቅ ተፈናቃዮች ለምግብ እጥረት እንዲጋለጡ ሳያደርግ አልቀረም። በተቃራኒው መንግሥት የምግብ እርዳታ ፈላጊው ቁጥር እጅግ መቀነሱን መግለፁ ይሰማል። ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ተከስቶባት የነበረዉን ከፍተኛ ረሃብ እና ድርቅ ከዓለም ደብቃ ሳለ በግብረሰናይ ድርጅቶች እና ጋዜጠኞች ለአደባባይ መብቃቱ ይታወቃል።የአማራ ክልል ተፈናቃዮች አቤቱታ
ዛሬስ? በርግጥ ኢትዮጵያ ዉስጥ የምግብ እጥረት አለ? ኢትዮጵያ በተከታታይ ድርቅ እንደሚጋጥማት ይታያል፤ ዛሬ የምግብ ዋስትናዋ ምን ያህል አስተማማኝ ነዉ? ዓለምን አስተባብሮ ለእርዳታ ካስነሳው ከዛሬ 40 ዓመት ወዲህ ምን አይነት መሻሻል እና ለዉጥስ ታይቷል? በእነዚህ ነጥቦች ላይ ሃሳባቸዉን ያካፍሉን፤“በቡግናና ዋግኽምራ በምግብ እጥረት ህፃናት እየሞቱ ነው” ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
1-አቶ አሊ ሰዒድ - የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ፤
2,-አቶ ምህረት መላኩ የዋግ ህምራ ብሔረሰብ ዞን አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም አስተባባሪ ፤
3-ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በደርግ ዘመነ ሥልጣነ ፤ የእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚሽን፤ እንዲሁም የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የነበሩ እና ከፍተኛዉን ድርቅ በቅርበት የተከታተሉ፤ እንዲሁም
4, ዶ/ር አክሎክ ቢራራ - በልማት ጉዳይ የኤኮኖሚ ምሁር ናቸዉ።
ተወያዮች ሃሳባችሁን ቀርበዉ ስላካፈሉን በማመስገን፤ ሙሉዉን ዉይይት የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን!
አዜብ ታደሰ