ወደ ጀርመን ተመላሾች የኮሮና ምርመራ ሊደረግላቸዉ ነዉ
ዓርብ፣ ሐምሌ 17 2012ማስታወቂያ
ዉጪ ሐገር ሰንብተዉ ወደ ጀርመን የሚመለሱ ጀርመናዉያንና የጀርመን ነዋሪዎች በየሚደርሱበት አዉሮፕላን ማረፊያ የኮሮና ተሕዋሲ ምርመራ እንዲደረግላቸዉ የሐገሪቱ የጤና ባለስልጣናት ወሰኑ።የሰሜኑ ንፍቀ-ክበብ በጋ የዕረፍት ጊዜ በመሆኑ ለጉብኝት ዉጪ ሐገር ሰንበተዉ የሚመለሱ መንገደኞች በየሔዱበት በኮሮና ተሕዋሲ ይያዛሉ፣ሲመለሱ ደግሞ ተሕዋሲዉን ያዛምታሉ ተብሎ ይፈራል።የጀርመን የፌደራልና የ16ቱ ክፍለ-ሐገራት የጤና ሚንስትሮች ዛሬ ባደረጉት ዉይይት ማብቂያ በተለይ ተሕዋሲዉ በብዛት የተሰራጨባቸዉ ሐገራትን ጎብኝተዉ የሚለሱ በየሚደርሱበት አዉሮፕላን ጣቢያ ምርመራ እንዲደረግላቸዉ ወስነዋል።በሚንስትሮቹ ዉሳኔ መሠረት ተሕዋሲዉ ብዙም ካልተሰራጨባቸዉ ሐገራት የሚመለሱት ግን ምርመራ የሚደረግላቸዉ መንገደኞቹ ከፈቀዱ ነዉ።ምርመራዉ ለሁሉም የሚደረገዉ በመንግሥት ወጪ ነዉ።የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት ጀርመንና በአብዛኞቹ የአዉሮጳ ሐገራት ቀንሷል።
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ