አውርጳን ያሳስቡት ፕሬዝዳንት ትራምፕ
ረቡዕ፣ ጥር 14 2017ከትናንት ወዲያ በተክበረው በአለ ሹመት ለሁለተኛ ግዜ ወደኋይት ሃውስ የመጡት 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሌላው የዓለም ክፍል ይልቅ በአውሮፓ አነጋጋሪና ትኩረት ሳቢም ሁነዋል። አሜሪካና አውሮፓ ነባር ወዳጆችና አጋሮች ከመሆን አልፎ አለምን በጋራ ሲያሾሩና ሲመሩ የነበር መሆኑ የሚታውቅ ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት ትራም ግን አውሮፓ አሚሪካንን ለአመታት ያላግባብ ሲጠቀምባት እንደነበር በመግለጽ ይህን ሁኔታ እንደሚለውጡ ቃል በመግባት ወደ ስልጣን መምታቸው ነው ፕሬዝዳንቱን በአውሮፓ አነጋጋሪና አሳሳቢም ያደረጋቸው።፡
የፕሬዝዳንቱ የአሜሪካ ትቅደም ፖሊሲ ምንነትና አንደምታው
ፕረዝዳንቱ ቅድሚያ ለአሜሪካ በሚለው መፍክራቸው ዳግም ከተመረጡ ወዲህ የአውሮፓና አሜርካ ቀጣይ ግንኑነትና አብሮነት እንዴትነት ሲያነጋግር ቆይቷል። ባለፈው ሰኞ በአለ ሹመታቸው ያሰሙት ንግግርና ያስተላለፉቸው ትዛዞች የፕሪዝዳንቱ አዳዲስ አስተሳሰቦች መተግበር መጀምራቸውን የሚያመላክቱ ሁነዋል።
ፕረዝዳንቱ አሜሪካ ባለፉት አመታት ከራሷና ከህዝቧ ይልቅ ለሌሎች በተለይም ላውሮፓውያን ስትሰራና ስትጠቅም እንደቆየች በመግለጽ፤ ከእንግዲህ ግን ቅድሚያ ለራሷ እንደምትሰጥና አሚሪካንን የማይጠቅሙ ወይንም ደግሞ ብዙ ወጭ የሚያሰወጡ ባሏቸው ያለም የጤና ድርጅትና የአየር ነብረት ለውጥ የመሳሰሉ ስምምነቶች አገራቸው እንድትወጣ የሚያስችሉ ትዝዞችን አስተላለፈዋል።የፕሬዚዳንት ትራምፕ የውጭ ግንኙነት መርሆች
የማንንም ጦርነት የማትዋጋዋ አሜሪካ
አሜርካ የራሷን ደንበር ማስጠበቅና ግዛቷንም ማስፋፋት እንጂ የማንንም የሌላ ደንበር የማታስከብርና የማንንም ጦርነት የማትዋጋ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ግልጽ አድርገዋል። ፡” በዓለም ጠንካራ የተባለውን ወታደራዊ ሀይል እንገነባለን. ስኬታችንን የምንለካውም በምናሸንፋቸው ጦርነቶች ብቻ ሳይሆን በምንቋጫቸውና ምናልባትም ወደጦርነትም ባለመግባት ጭምር ነው” በማለት እሳቸው በግል ጦርነቶችን በማስወገድና ሰላምን በማስፈን ሊታወቁ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።
አሜሪካና አውሮፓ በስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ የተሳሰሩና በዓለም ትልቁን የጦር ሀይል የገነቡ ቢሆንም የዚህ የጦር ድጅርት ዋናዋ ሀይልና የገንዘብ ምንጭ ግን አሚሪካ ናት። ፕሬዝዳንት ትራም ሁሉም አባል አገር የበኩሉን ካላዋጣ ከድርጅቱ እንደሚወጡ ሲገልጹ ቆይተዋል።
በበዓለ ሹመቱ ከአውሮጳ የተገኙ ባልስልጣኖች
በሰኞው የፕሬዝዳንቱ በዓለ ሹመት ከጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስተር ጆርጂያ ሜሎኒ በስተቀር የጀርመን፣ የፈረንሳይ ወይም የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣኖች አልተጋበዙም። ይልቁንም በበአሉ የታደሙት የአውሮፓ አክራሪ ቀኝ ፖለቲከኞችና ብሄረተኖች መሆናቸው ቀጣዩን የአውሮጳና አሜካንን ግንኙነት ውስብስብ እንዳይደርገው አስግቷል ።
በንግድ የሚፈጠረው ውዝግብ አይቀሬነት
ትራምፕ ዳግም ሊመረጡ መቻላቸው በአውሮጳ ያሳደረው ስጋት
ፕሬዝዳንትትርምፕ ከውሮፓ ጋር ያለው የንግድ ጉድለት በማንሳትም፤ “ የአውሮፓ ህብረት ለኛ ጥሩ አይድለም ጎድቶናል ። መኪኖቻንንም ሆነ የግብርና ምርቶቻችንን አይወስዱም ስለዚህ ይህን ለማስተካከል ብቸኛው መንገድ በነሱ ሸቀጦች ላይ ተጨሚሪ ታክስ መጣል ነው” በማለት በሁለቱ ወገኖች ንግድ ሊነሳ የሚችለውን ውዝግብ አመላክተዋል።
አውሮፓ በሰፊው በገባበት የዩክሬን ጦርነት ላይም ፕሬዝዳንቱ አገራቸው ለጦርነቱ የምትሰጠው ድጋፍ ሊቀጥል እንደማይይችል በመገለጽ ጦርነቱ መቆም እንዳለበትና ለዚህም እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።በጦርነቱ የማስቆሚያ ስልት ላይ ግን ስምምነት ያለ አይመስልም።
የአውሮጳና አሜሪካንን ወዳጅነትን ማስቀጠል
በአውሮጳና በፕሬዝዳንት ትራምፗ አሜርካ መካከል ያለው ፍጥጫና ልዩነት ሰፊ ሲሆን ይህም ትልቁ የወቅቱ ፈተና ሁኗል። ቀድሞ የኔቶ ዋን ጸሀፊ የነበሩት ጃን ስቶልስቴንበርግ ግን ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባትና ልዩነት በብልሀት በመያዝ የአትላንቲክ ማዶና ማዶ ግንኑነቱን ማስቀጠል እንደሚገባ ይመክራሉ። “ ከዚህ ቀደ ስንሰራ እንደነበረው እንዲያደርጉ እመክራለሁ።ጋደኛሞች ቁጭ ብለው ሊወያዩና ሊግባቡ ይገባል” ከዚህ ውጭ ያለው መንገድ ለሁለቱም የማይጠቅም መሆኑን አስገንዝበዋል ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ