የእስልምና እምነት ተከታዮች የረመዳን ወርን እንዴት አሳለፉ?
ቅዳሜ፣ ግንቦት 15 2012ማስታወቂያ
1441ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ በመላው ዓለም ይከበራል። በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የረመዳን የጾም ወር አሁን አብቅቷል። የረመዳን ወር በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ እምነቱ የሚያዘውን የተለያዩ ተግባራት ከመከወን ባሻገር በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎት ላይ ተሳታፊ በመሆን ጭምር አልፏል። እዚህ ጀርመን የሚኖሩ ከተለያዩ የዓለም ሃገራት የመጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች የረመዳን የጾም ወቅትን እንዴት እንዳሳለፉ ዶይቸ ቬለ አነጋግሯቸዋል።
እንዳልካቸው ፈቃደ
ታምራት ዲንሳ