በጀርመን ሁለተኛው የኮሮና ተሐዋሲ ማዕበል ስጋት
ረቡዕ፣ ጥቅምት 4 2013ማስታወቂያ
ጀርመን ዉስጥ ሰሞኑን በቀን እስከ 5000 የሚደርስ ሰዉ በኮሮና ተሕዋሲ መያዙ አዲስ ስጋት አስከትሏል።ሰሞኑን የተያዘዉ ሰዉ ቁጥር ከሚያዚያ ወዲሕ ከፍተኛዉ ነዉ። መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከሀገሪቱ 16 የፌደራል ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትሮች ጋር ጠበቅ ያለ የመከላከል ርምጃ ለመውሰድ ሲመክሩ ውለዋል። ከባለሥልጣናቱ ውይይት በኋላም በአንድ ቦታ መሰብሰብ የሚችሉ ሰዎች ቁጥር፣ በግለሰብ ደረጃ የሚዘጋጁ ድግሶች፣ የምግብና መጠጥ ቤቶች መዝጊያ ሰዓት እና የመሳሰሉትን የተመለከተ መመሪያ እንደሚወጣ ይጠበቃል። እስካሁን በመገበያያ ስፍራዎችና በሕዝብ መጓጓዣዎች ላይ ግዴታ የነበረው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፤ በሌሎች ስፍራዎችም እንዲደረግ ውሳኔ ሊተላለፍ እንደሚችልም ተጠቁሟል። ሁለተኛው የኮሮና ተሐዋሲ ማዕበል ስጋት በጀርመን ምን ይመስላል?
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ