በዋግህምራ በድርቅና በምግብ እጥረት እየተፈናቀሉ ያሉት አርሶደሮች
ሰኞ፣ ግንቦት 18 2017በዋግ ህምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር በድርቅና በምግብ እጥረት እየተፈናቀሉ ያሉት አርሶደሮች
በአማራ ክልል በዋግ ህምራ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር በድርቅና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት በተፈጠረ የምግብ እጥረት አርሶደሮች አካባቢያቸዉን እየለቀቁ መሆኑ ተነገረ።
ወ/ሮ ኪሮስ ወልዴ በዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጻግምጅ ወረዳ ኗሪ ናቸው ባለቤታቸውን ጨምሮ 7 የቤተሰቡ አባላት በአካባቢው በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ጋር ተያይዞ ህጻናት ልጆቻቸውን ይዘው ደሴ ከተማ ምጽዋት በመጠየቅ ህይወታቸውን ይመራሉ። ኪሮስ ወልዴ እባላለሁ ከሰቆጣ ጻግምጅ ነው የመጣሁት እንጀራ የለም ችግር ነው ደሃ ነን እርዳታ አለ ትንሽ ትንሽ በመሀበል ነው የሚሰጡን ባሌም አለ 7 የቤተሰብ አባላት ነው የመጣነው”በድርቅና ረሃብ ለተጎዱ ወገኖች እርዳታ የማሰባሰቢያ ዘመቻ
የአርሶደሮች መፈናቀል
ተደጋጋሚ የሆነ የተፈጥሮ አደጋ የሚከሰትበት በአማራ ክልል ዋግህምራ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር በ2016ዓ.ም በሳህላ ወረዳ አሁን በያዝነው አመት ደግሞ በዳህና ዛጊብላ ጻግምጅ ፣ ሰቆጣ፣ አበርገሌ ፣ እና ዝቋላ አካባቢ በተከሰተ ድርቅ እና ተፈጥሮአዊ አደጋ ምክንያት 118,000 (አንድ መቶ አስራ ስምንት ሽህ) ሰዎች የእለት ምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሆኗል ከ20,000 በላይ የለት ደራሽ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ነዋሪዎ ያሉበት የጻግምጅ ወረዳም ማህበረሰቡን በደረሰው ተፈጥሮአዊ አደጋ ምክንያት ምግብ ስለሌለው ወደተለያ ቦታዎች ለስደት እንደተዳረገ የወረዳ ግብርና ልማት ኃላፊ አቶ ስዩም አባቴ ይናገራሉ፡፡በዋግህምራ ሁለት ወረዳዎች «ሰሚ አጥተዋል» መባሉ
“ከዚህ በፊት በነበረ ድጋፍ እና በራሳቸው ጥረት ነው አካባቢው ላይ ሲኖሩ የነበሩት ነገር ግን አሁን ይህ በመቆሙ ምክንያት ማህበረሰቡ ለስደት ፣ ለችግር፣ ለእንግልት ተዳርጓል፡፡ ልጆቻቸውን ይዘው ነው የሚሄዱት ምንም አይነት የሚቀመስ ስለሌለ”
የተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥ
በዞኑ በሚገኝ አንድ ት/ቤት መምህር እንደሆኑ የነገሩኝ እና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አስተያየት ሰጭም አሁን በአካባቢው ባለው የምግብ እጥረት ምክንያት ከ1 ት/ቤት እስከ 160 ተማሪዎች ያቋርጣሉ ብለዋል፡፡ “ኃይለኛ ስደት አለ የሚሄዱት ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ወደ ወሎ አካባቢ ነው ከአንድ ት/ቤት ከ100 እስከ 160 የሚደርሱ ተማሪዎች የሚያቋርጡ አሉ ምክንያቱም የምንበላው የለም በሚል ሰበብ ነው፡፡”
ማህበረሰቡም በየጊዜው በሚፈጠሩ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ምክንያት የሚደርስበትን ችግር መፍትሄ ለመስጠት የተሄደበት እርቀት ጊዜያዊ እና በእርዳታ ላይ ያተኮረ በመሆኑ በዘላቂነት ከችግር ሊወጣ አልቻለም በማለት አቶ ስዩም አባቴ ይገልጻሉ።
የሚወሰዱ እርምጃዎች ጊዜያዊ መሆን
“እኛ የወሰድናቸው እርምጃዎች ያን ያህል ይህን ማህበረሰብ ከስደት ሊያስቀር አልቻለም ማህበረሰቡ ብዙ ትኩረት የሚፈልግ ነው። መንግስትም በዘላቂነት ችግር ሊፈታ የሚችል ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደስራ መግባት አለበት”የአበርገሌና የጻግብጂ ወረዳ ነዋሪዎች ሮሮ
በዋግህምራ ብሄረሰብ ዞን የአሜሪካ ተራዶ ድርጅት ስራ አቁሞ በነበረባቸው ጊዜቶች የእለት ምግብ ድጋፍ ያልነበራቸዉ አካባቢውን ለቀው ተንቀሳቅሰዋል የሚሉት የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ አሁን የአሜሪካ ተራዶ ድርጅት የምግብ ድጋፍ ማቅረቡ ጋር ተያይዞ አካባቢውን ለቀው የነበሩ አርሶአደሮች እየተመለሱ ነው ይላሉ።
“በአጋጣሚ ሆኖ ዩ.ኤስ.አይ.ዲ የተሰኘ ድርጅት ድጋፍ አቁሞ ነበር በዚህ ምክንያት ወደ ሌላ አካባቢ የሚጓዙ አርሶአደሮች ነበሩ አሁን ፕሮግራን አስተካክለን በሁሉም ወረደ ከዝቋላ ወረዳ ውጭ በዋግ ህምራ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር ምላሽ መስጠት ስለጀመርን አሁን የምትላቸው ሰዎች 1፣2፣3 ሰዎች አነስተኛ ቁጥር እንቅስቃሴ ካልሆነ ወደ አካባቢያቸው መተዋል፡፡”
አሁን ላይ እየቀረበ ባለው ድጋፍ ማህበረሰቡ ባለበት እንዲቆይና የወጡ እንዲመለሱ በማድረግ የማረጋጋት ተግባር ተሰርቷል የሚሉት አቶ ምህረት አሁን ችግር የለም ማለት ባይቻልም ቀጠናውን ግን ማረጋጋት ተችሏል ሲሉ ይገልፃሉ ፡፡
“118ሽ የሚሆኑ ከጠየቅነው 60በመቶ ድጋፍ እየተደረገልን ነው በተለያዩ ግብረሰናይ ደርጅቶች ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ ግን ከወትሮው እቀነሰ ነው ፡፡ ችግር የለም ብለን ባናጠቃልለውም በማረጋጋት ደረጃ የተሸለ ቀጠና እንዲሆን አድርጎታል”
በዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በ2 ከተማ አስተዳደር እና በሰባት የገጠር ቀበሌዎች 118ሽ የሚደርሱ ሰዎች የእለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡
ኢሳያስ ገላዉ
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ