በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ውዝግብ ላይ የባለሙያዎች አስተያየት
ሐሙስ፣ ግንቦት 21 2017ከሰሞኑ በኤርትራ 34ኛው የነጻነት በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ብዙ ስለተባለለት የቅርብ ጊዜውን የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከርን ይበልጡኑ ገሃድ ያወጣው ጉዳይ መስሏል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰባት ዓመታት በፊት የመጣውን መንግስታዊ ለውጥ ተከትሎ ፍጹም መሻሻል አሳይቶ የነበረው የአስመራ እና አዲስ አበባ ግንኙነት ከደም አፋሳሹ የሰሜን ጦርነት መቋጨት በኋላ ግን ወደ ነባር ይዞታው የተመለሰ ስመስል ቆይቶ ባለፉት ሁለት ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ መሻከሩ በሂደት በግልጽ እየታየ መጥቷል፡፡
የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደ መዘዝ...
የፖለቲካል ሳይንስ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰለሞን ተፈራ ሰሞነኛውን የፕሬዝዳት ኢሳያስ ንግግርን አስታከው ለዶይቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት የኤርትራን መንግስት በፀብ አጫሪነት በመክሰስ ነው፡፡ “ኢሳያስ ካደረጉት ንግግሮች አብዛኛውን ስለ ኢትዮጵያ እና ሌሎች አገራት በማውራት ነው የጨረሱት” ያሉት ሰለሞን የኤርትራ መንግስት የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መቋጨትን ተከትሎ ባሳየው ኩርፊያ በኢትዮጵያ ታጥቀው መንግስትን የሚወጉ አማጺያንን በመደገፍ ፀብ አጫሪነቱን ያሳየ ነው በማት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያና ኤርትራ ዳግም ጦርነት ይገጥሙ ይሆን? የፕሬዝደንት ኢሳያስ መልዕክት፣ የፖለቲካ ተንታኝና የፖለቲከኛ አስተያየት
መቀመጫቸውን ለንደን ያደረጉት ትውለደ ኤርትራዊ የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ተንታኝ አብዱራሃማን ሰይድ ግን እየሻከረ የመጣው የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ምክንያት ከዚያም ሳይሻገር አይቀርም የሚል አስተያየት ነው ያላቸው፡፡ “በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተነሳው የባህር አጠቃቀም ጉዳይ ጦርነትን እንደማንሳት ነበርና የታየው ከዚያም ደግሞ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ሚና መፈተሽ ያለበት ጉዳይ ይመስላል፤ ምክንያቱም ኢምሬቶቹ በሱዳን የፈጥኖ ደራሹን ኃይል ስደግፍ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ደግሞ ከመደበኛ ጦሩ ጋር ናቸውና ኢሳያስ ዐቢይ ላይ አሳይተው የነበረውን ትልቅ እምነት በመጠቀም የውሃውም ጉዳይ መፍታት ይችሉ የነበረ ብሆንም የኢምሬቶች ሚና በጥልቁ መፈተሽ ያለበት ነው” ሲሉ መላምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
የኦሮሞ ልሒቃንን ያስቆጣው የኤርትራው ፕሬዝዳንት ንግግር
የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት ለኤርትራ ስጋት ነውን?
ተንታኞቹ የሁለቱ አገራት ቀጣይ እጣፈንታና ስላንዣበበው ስጋትም በሰጡት አስተያየት ጦርነትን ማስቀረት የሚቻልበት እድሉ ሰፊ መሆኑን አንስተዋል፡፡ አቶ አብዱራሃማን “የወደብ አገልግሎት የጋራ ትቅም ስላለበት ብዙ የሚያስቸግር አይመስሊም” በማለት ምናልባት ወደ ግጭት ልወስድ የሚችለው ጉዳይ ግዛቶቹን መጠቅለል ጉዳይ ነው ሲሉ አቶ ሰለሞን በፊናቸው፤ “ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ፍላጎቷን በግልጽ ስታሳይ ባህር በር የማገኘው በኤርትራ በኩል ነው አላለችም” በማለት ቢሆንም እንኳ ግን ጥቅሙ ለሁለቱ መንግስታትና ህዝብ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት አቋም
ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢህ አህመድ የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎትን በማስመልከት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የመንግስታቸውን አቋም ስያስረዱ ይህን ማለታቸው አይዘነጋም፤ “አሁን ከኤርትራ ጋራ አንዳንድ ወሬ ይነሳል፡፡ የምንፈልገው ሰላም ነው፡፡ ከዚያ የከፋ ነገር ካልመጣ በኛ ተነሳሽነት በኤርትራ ወንድሞቻችን ላይ ምንም የሚፈጸመው ነገር የለም” በማለት ነገር ግን መንግስታቸው የቀይ ባህር አገልግሎትን በሰላማዊ መንገድ ለማግኘት የማያወላዳ አቋም መኖሩን ማስረዳታቸው አይዘነጋም፡፡
ሥዩም ጌቱ
እሸቴ በቀለ
ታምራት ዲንሳ